Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘፀአት 19:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 አሁንም እነሆ፥ ለእኔ ብትታዘዙና ቃል ኪዳኔንም ብትጠብቁ ምንም እንኳ ምድር ሁሉ የእኔ ብትሆን የተለያችሁ ሕዝብ ትሆናላችሁ፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 አሁንም በፍጹም ብትታዘዙኝና ቃል ኪዳኔን ብትጠብቁ እነሆ ከአሕዛብ ሁሉ እናንተ የተወደደ ርስቴ ትሆናላችሁ፤ ምንም እንኳ ምድር ሁሉ የእኔ ብትሆንም፣

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 አሁንም ቃሌን በእውነት ብትሰሙ ኪዳኔንም ብትጠብቁ፥ ምድር ሁሉ የእኔ ናትና ከአሕዛብ ሁሉ የተመረጠ ርስት ትሆኑልኛላችሁ፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 አሁ​ንም ቃሌን በእ​ው​ነት ብት​ሰሙ፥ ኪዳ​ኔ​ንም ብት​ጠ​ብቁ፥ ምድር ሁሉ የእኔ ናትና ከአ​ሕ​ዛብ ሁሉ የተ​መ​ረጠ ርስት ትሆ​ኑ​ል​ኛ​ላ​ችሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 አሁንም ቃሌን በእውነት ብትሰሙ ኪዳኔንም ብትጠብቁ፥ ምድር ሁሉ የእኔ ናትና ከአሕዛብ ሁሉ የተመረጠ ርስት ትሆኑልኛላችሁ፤ እናንተም የካህናት መንግስት የተቀደሰም ሕዝብ ትሆኑልኛላችሁ።

Ver Capítulo Copiar




ዘፀአት 19:5
54 Referencias Cruzadas  

እንደገናም እግዚአብሔር አብርሃምን እንዲህ አለው፤ “አንተና ከአንተም በኋላ የሚመጣው ዘርህ ከእኔ ጋር የገባኸውን ቃል ኪዳን ከትውልድ እስከ ትውልድ ጠብቁ፤


እግዚአብሔር አምላክ ሆይ! የቀድሞ አባቶቻችንን ከግብጽ ምድር ባወጣህ ጊዜ ከዓለም ሕዝብ ሁሉ መካከል እስራኤልን የራስህ ሕዝብ እንዲሆን የመረጥከው መሆኑን በአገልጋይህ በሙሴ አማካይነት ተናግረሃል።”


እስራኤልን ዘለዓለም የራስህ ሕዝብ አደረግህ፤ እግዚአብሔር ሆይ፥ አንተም አምላካቸው ሆንክ።


ከሰማይ በታች ያለው ነገር ሁሉ የእኔ ነው፤ ታዲያ፥ እንድመልስለት ለእኔ ያበደረ ማነው?


ምሕረት እንድታደርግለት ይለምንሃልን? በመልካም አነጋገር ይለምንሃልን?


እግዚአብሔር ያዕቆብን ለራሱ፥ የእስራኤልንም ሕዝብ የግሉ አድርጎ መረጠ።


ምድርና በምድር ላይ የሚኖሩ ሁሉ፥ የእግዚአብሔር ናቸው፤ ዓለምና በውስጥዋ ያሉት ሁሉ የእርሱ ናቸው።


የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን ትእዛዞች ለሚጠብቁ ሰዎች የእግዚአብሔር መንገዶች ሁሉ ፍቅርና ታማኝነት ናቸው።


እንዲህም አላቸው፤ “በጥሞና ትእዛዞቼን ብታዳምጡና በፊቴ መልካም የሆነውን ነገር በታዛዥነት ብታደርጉ፥ ኅጎቼንም ሁሉ ብትጠበቁ፥ በግብጻውያን ላይ ካመጣሁባቸው በሽታዎች በአንዱ እንኳ አልቀጣችሁም፤ ፈዋሻችሁ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።”


ለእርሱ ብትታዘዝና እኔ ያዘዝኩህንም ሁሉ ብትፈጽም ጠላቶችህን እጠላለሁ፤ ተቃዋሚዎችህንም እዋጋለሁ፤


ከዚህ በኋላ የቃል ኪዳኑን መጽሐፍ ወስዶ ድምፁን ከፍ በማድረግ ለሕዝቡ አነበበ፤ ሕዝቡም “ለእግዚአብሔር እንታዘዛለን እርሱ ያዘዘውንም ሁሉ እንፈጽማለን” አሉ።


እንዲህም አለ፦ “እግዚአብሔር ሆይ፥ በአንተ ዘንድ ሞገስን አግኝቼ ከሆነ ከእኛ ጋር አብረህ እንድትወጣ እለምንሃለሁ፤ ይህ ሕዝብ እልኸኛ ነው፤ ነገር ግን ኃጢአታችንንና ክፉ ሥራችንን ሁሉ ይቅር በል፤ የራስህ ሕዝብ አድርገህ ተቀበለን።”


የእኔ ሕዝብ አደርጋችኋለሁ፤ እኔም አምላካችሁ እሆናለሁ፤ ከግብጽ ባርነትም ነጻ በማወጣችሁ ጊዜ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ መሆኔን ታውቃላችሁ፤


ነገር ግን በዚህ ምድር መካከል እኔ እግዚአብሔር መገኘቴን ታውቅ ዘንድ በዚያን ቀን ሕዝቤ የሚኖርባትን የጌሴምን ምድር ከዝንቦቹ መንጋ ነጻ አድርጌ እለያታለሁ።


ሙሴም ንጉሡን እንዲህ አለው፤ “ከከተማው እንደ ወጣሁ እጄን ዘርግቼ ወደ እግዚአብሔር እጸልያለሁ፤ ነጐድጓዱም ይቆማል፤ በረዶም ከእንግዲህ ወዲህ አይኖርም፤ በዚህ ዐይነት አንተም ምድር የእግዚአብሔር እንደ ሆነች ታውቃለህ።


እኔ የግሌ የሆነ የወይን ተክል ቦታ አለኝ፤ ሰሎሞን ሆይ! አንተ አንድ ሺህ ብር፥ አትክልተኞቹ ሁለት መቶ ብር ልትወስዱ ትችላላችሁ።


እሺ ብላችሁ ብትታዘዙኝ ምድር የምታስገኘውን በረከት ትበላላችሁ፤


“ነገር ግን አንተ አገልጋዬ እስራኤል ሆይ! ሕዝቤ እንድትሆን የመረጥኩህ የወዳጄ የአብርሃም ዘር ነህ።


የያዕቆብ ልጆች እስራኤላውያን ሆይ! የፈጠራችሁ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የታደግኋችሁ ስለ ሆነ አትፍሩ፤ እናንተ የእኔ ናችሁ፤ በስማችሁም ጠርቼአችኋለሁ።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ሰንበቴን ለሚያከብሩ፥ እኔ የምፈቅደውን ነገር ለሚመርጡና፥ በቃል ኪዳኔ ለሚጸኑ ጃንደረቦች


የያዕቆብ አምላክ ግን እንደ እነርሱ አይደለም፤ እርሱ የሁሉ ነገር ፈጣሪ ነው። እስራኤልንም የራሱ ሕዝብ እንዲሆን መርጦታል፤ ስሙም የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ነው።


መታጠቂያ በወገብ ዙሪያ ተጣብቆ እንደሚገኝ፥ የይሁዳና የእስራኤል ሕዝብ ከእኔ ጋር እንዲጣበቁ ዐቅጄ ነበር፤ ይህንንም ያደረግኹት ሕዝቤ እንዲሆኑና ለስሜ ምስጋናና ክብር እንዲያስገኙ ነበር፤ እነርሱ ግን አልሰሙኝም።”


ነገር ግን እኔ አምላካቸው ስሆን እነርሱም ሕዝቤ ይሆኑ ዘንድ ለእኔ መታዘዝ እንደሚገባቸው ብቻ ነገርኳቸው፤ ሁሉ ነገር እንዲከናወንላቸው ከፈለጉም እኔ በሰጠኋቸው ሥርዓት እንዲኖሩ አዘዝኳቸው።


“እንደገናም በአጠገብሽ ሳልፍ ጊዜሽ የፍቅር ዕድሜ ነበር፤ የተራቈተውን ሰውነትሽንም በመጐናጸፊያዬ ሸፍኜ ቃል ገባሁልሽ፤ ከአንቺም ጋር እንደ ጋብቻ ያለ ቃል ኪዳን ገብቼ የእኔ የግሌ አደረግሁሽ፤” ይህን የተናገረ ልዑል እግዚአብሔር ነው።


ነገር ግን ምድራቸውን ትወርሳላችሁ፤ በማርና በወተት የበለጸገችውን ምድር እንድትወርሱ እሰጣችኋለሁ፤ ከሌሎች ሕዝቦች እንድትለዩ ያደረግኋችሁ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ።


“በዓለም ከሚኖሩ ሕዝቦች ሁሉ እኔ የመረጥኩት እናንተን ብቻ ነው፤ በምትሠሩት ኃጢአት ሁሉ የምቀጣችሁ ስለዚህ ነው።”


የእስራኤል ሕዝብ ርዳታቸውን ፈልጎ ወደ መሪዎቹ ይመጣል፤ እነርሱ ግን በጽዮን ተዝናንተው ስለሚቀመጡና በሰማርያ ተራራ ላይ ያለ ሥጋት ስለሚኖሩ ለእነዚህ ታዋቂ መሪዎች ወዮላቸው!


የሠራዊት አምላክ እንዲህ ይላል፦ “እነርሱ የእኔ ይሆናሉ፤ እኔ በምሠራበት ቀን እነርሱ የእኔ የግሌ ይሆናሉ፤ ወላጆች ለሚያገለግሉአቸው ልጆች ምሕረት እንደሚያደርጉላቸው እኔም ለእነርሱ ምሕረት አደርግላቸዋለሁ።


“ምድርና በእርስዋም ያለው ሁሉ የጌታ ነው።”


ነገር ግን አንድ ሰው “ይህ ሥጋ ለጣዖት የተሠዋ ነው” ቢላችሁ ይህን በነገራችሁ ሰው ምክንያትና በኅሊናም ምክንያት ሥጋውን አትብሉ።


ሰማይና ከሰማይ በላይ ያሉ ሰማያት፥ ምድርና በእርስዋም ላይ ያለው ማናቸውም ነገር ሁሉ የእግዚአብሔር ነው።


ዛሬ እኔ የምሰጣችሁን የእግዚአብሔር አምላካችሁን ትእዛዞች ሁሉ ብትፈጽሙ በረከት ታገኛላችሁ፤


አንተ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር የተለየህ ሕዝብ ነህ፤ በምድር ላይ ከሚኖሩ ከሌሎች ሕዝቦች መካከል ለእርሱ የተለየህ ሕዝብ ትሆን ዘንድ ለራሱ መርጦሃል።


“ሞቶ የተገኘውን እንስሳ አትብላ፤ በመካከልህ የሚኖሩ የውጪ አገር ሰዎች እንዲመገቡት ፍቀድላቸው፤ ወይም ለውጪ አገር ሰዎች በዋጋ ልትሸጥላቸው ትችላለህ። አንተ ግን ለአምላክህ ለእግዚአብሔር የተለየህ ሕዝብ ነህ። “የፍየልን ግልገል በእናቱ ወተት አትቀቅል።


ስለዚህም እግዚአብሔር በሰጠህ ተስፋ መሠረት እነሆ፥ ዛሬ ለእርሱ የተለየህ ውድ ሕዝብ አድርጎ ተቀብሎሃል፤ ትእዛዞቹንም ሁሉ እንድትፈጽም ያዝሃል፤


ይህን ብታደርግ ከፈጠራቸው ሕዝቦች ሁሉ በላይ በምስጋና፥ በስም፥ በክብርም ከፍ ሊያደርግህና በሰጠውም ተስፋ መሠረት ለእርሱ የተለየህ ሕዝብ እንደሚያደርግህ ነግሮሃል።”


“ለአምላክህ ለእግዚአብሔር ብትታዘዝና ዛሬ እኔ የምሰጥህንም ትእዛዞች ሁሉ በታማኝነት ብትጠብቅ፥ በምድር ላይ ከሚኖሩ ሕዝቦች ሁሉ በላይ ከፍ ከፍ ያደርግሃል፤


“ለአምላክህ ለእግዚአብሔር ብትታዘዝና ትእዛዞቹንም ሁሉ ብትፈጽም በተስፋ ቃሉ መሠረት ለራሱ የለየህ ወገን ያደርግሃል።


እናንተ ግን እሳት እንደሚነድበት የብረት ምድጃ ከሆነችው ከግብጽ መንጥቆ እግዚአብሔር ያወጣችሁ ዛሬ እንደ ሆናችሁት ሁሉ ለራሱ የተለያችሁ ወገኖቹ እንድትሆኑ ነው።


እግዚአብሔር አምላካችን በሲና ተራራ ላይ ቃል ኪዳን አደረገ፤


አንተ እግዚአብሔር አምላክህ የራሱ ወገን አድርጎ የመረጠህ ቅዱስ ሕዝብ ነህ፤ በምድር ላይ ካሉት ሕዝቦች ሁሉ አንተ ለእርሱ የተለየህ ምርጥ ሕዝብ እንድትሆን አድርጎሃል።


ከዚህም ሁሉ በላይ ይህ ሕዝብ ለራስህ ወገን እንዲሆን የመረጥከውና በታላቁ ኀይልህና ብርታትህ ከግብጽ ምድር ያወጣኸው ነው።”


ክርስቶስ ከዐመፃ ሁሉ ሊያድነንና መልካም ሥራ ለመሥራት ትጉሆችና ለእርሱ የተለየን ንጹሕ ሕዝብ እንድንሆን ያነጻን ዘንድ ስለ እኛ ራሱን አሳልፎ ሰጠ።


አብርሃም ወጥቶ ርስት አድርጎ ወደሚቀበለው ስፍራ እንዲሄድ በተጠራ ጊዜ ምንም እንኳ ወዴት እንደሚሄድ ባያውቅም ለመሄድ የታዘዘው በእምነት ነው።


ይህም ቃል ኪዳን እጃቸውን ይዤ ከግብጽ ምድር ባወጣኋቸው ጊዜ ከአባቶቻቸው ጋር እንደ ገባሁት ቃል ኪዳን ያለ አይደለም፤ እነርሱ በቃል ኪዳኔ ስላልጸኑ እኔም ችላ አልኳቸው ይላል ጌታ።


ከዚህም በኋላ ሕዝቡ ኢያሱን “እኛ አምላካችንን እግዚአብሔርን እናመልካለን፥ ትእዛዞችንም እንፈጽማለን” አሉት።


እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚያስደንቅ ብርሃኑ የጠራችሁን የእግዚአብሔርን አስደናቂ ሥራ እንድታውጁ የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት፥ እግዚአብሔር ለራሱ ያደረጋችኹ ቅዱስ ሕዝብ ናችሁ።


ሳሙኤልም እንዲህ አለ፤ “እግዚአብሔር የሚወደው የቱን ይመስልሃል? መታዘዝን ወይስ ቊርባንና መሥዋዕት ማቅረብን? ለእርሱ መታዘዝ ምርጥ የበግ መሥዋዕት ከማቅረብ ይበልጣል፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos