እርሱም፦ “ሂዱ፥ የሰባውን ብሉ፥ ጣፋጩንም ጠጡ፥ ለእነዚያ ምንም ላልተዘጋጀላቸው ድርሻቸውን ላኩ፤ ይህ ቀን ለጌታችን ቅዱስ ነውና፤ አትዘኑ የጌታ ደስታ ኃይላችሁ ነውና” አላቸው።
ዘካርያስ 14:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ያሉ ምንቸቶችም ሁሉ ለሠራዊት ጌታ የተቀደሱ ይሆናሉ። የሚሠውትም ሰዎች ሁሉ ይመጣሉ፥ በእነርሱም ውስጥ ይቀቅሉባቸዋል። በዚያም ቀን በሠራዊት ጌታ ቤት ከእንግዲህ ወዲያ ነጋዴ አይገኝም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ያሉ ምንቸቶች ሁሉ ለሰራዊት ጌታ ለእግዚአብሔር የተቀደሱ ይሆናሉ፤ መሥዋዕት ለማቅረብ የሚመጡ ሁሉ ምንቸቶቹን በመውሰድ ያበስሉባቸዋል፤ በዚያ ቀን በእግዚአብሔር ጸባኦት ቤት ከእንግዲህ ወዲያ ከነዓናዊ አይገኝም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ምድር የሚገኘው ማሰሮ ሁሉ ለሠራዊት አምላክ የተለየ ይሆናል፤ መሥዋዕት የሚያቀርቡ ሰዎች ሁሉ በማሰሮዎቹ ጥቂቱን የመሥዋዕቱን ሥጋ ያበስሉባቸዋል፤ በዚያን ጊዜ በሠራዊት ጌታ በእግዚአብሔር መቅደስ ውስጥ የሚነግድ ማንም ሰው አይኖርም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ያሉ ምንቸቶችም ሁሉ ለሠራዊት ጌታ ለእግዚአብሔር የተቀደሱ ይሆናሉ፣ የሚሠውትም ሰዎች ሁሉ ይመጣሉ ከእነዚያም ወስደው ይቀቅሉባቸዋል፣ በዚያም ቀን በሠራዊት ጌታ በእግዚአብሔር ቤት ከነዓናዊው ከእንግዲህ ወዲያ አይገኝም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ያሉ ምንቸቶችም ሁሉ ለሠራዊት ጌታ ለእግዚአብሔር የተቀደሱ ይሆናሉ፥ የሚሠውትም ሰዎች ሁሉ ይመጣሉ ከእነዚያም ወስደው ይቀቅሉባቸዋል፥ በዚያም ቀን በሠራዊት ጌታ በእግዚአብሔር ቤት ከነዓናዊው ከእንግዲህ ወዲያ አይገኝም። |
እርሱም፦ “ሂዱ፥ የሰባውን ብሉ፥ ጣፋጩንም ጠጡ፥ ለእነዚያ ምንም ላልተዘጋጀላቸው ድርሻቸውን ላኩ፤ ይህ ቀን ለጌታችን ቅዱስ ነውና፤ አትዘኑ የጌታ ደስታ ኃይላችሁ ነውና” አላቸው።
በዚያም አውራ ጎዳና ይኖራል፥ እርሱም የተቀደሰ መንገድ ይባላል፤ ንጹሐን ያልሆኑ አያልፉበትም፥ የእርሱ የሆኑ ሕዝቦች ግን ያልፉበታል፤ ተጓዦች ሆኑ፥ ሰነፎች እንኳ አይስቱበትም።
ጽዮን ሆይ፥ ተነሺ፥ ተነሺ፥ ኃይልሽን ልበሺ፤ ቅድስቲቱ ከተማ ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ያልተገረዘና ርኩስ ከእንግዲህ ወዲህ አይገባብሽምና ጌጠኛ ልብስሽን ልበሺ።
ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በእስራኤል ልጆች መካከል ያለ የባዕድ ልጅ ሁሉ፥ ልቡ ያልተገረዘ ሥጋው ያልተገረዘ የባዕድ ልጅ ሁሉ ወደ መቅደሴ አይግባ።
ርስት አድርጋችሁ ምድሪቱን በዕጣ በምታካፍሉበት ጊዜ ከምድሪቱ የተቀደሰውን ክፍል መባ አድርጋችሁ ወደ ጌታ ታቀርባላችሁ። ርዝመቱ ሀያ አምስት ሺህ ክንድ ወርዱም ሀያ ሺህ ክንድ ይሆናል፤ በዳርቻው ዙሪያ ሁሉ የተቀደሰ ይሆናል።
እኔም በተቀደሰው ተራራዬ በጽዮን የምቀመጥ ጌታ አምላካችሁ እንደሆንሁ ታውቃላችሁ፥ የዚያን ጊዜም ኢየሩሳሌም የተቀደሰች ትሆናለች፥ እንግዶችም ከእንግዲህ ወዲህ አያልፉባትም።
እዚያም እናንተ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁ፥ ወንዶችና ሴቶች አገልጋዮቻችሁ፥ እንዲሁም የራሳቸው ድርሻ ወይም ርስት የሌላቸው በየከተሞቻችሁ የሚኖሩት ሌዋውያን በጌታ በአምላካችሁ ፊት ሐሤት አድርጉ።”
በዚያም በጌታ በአምላካችሁ ፊት ትበላላችሁ፤ ጌታ አምላካችሁ እናንተን በባረከበት፥ በምታደርጉት ሁሉ አንተና ቤተሰቦችህ ሐሤት ታደርጋላችሁ።”
ይህ ሳይሆን ቀርቶ ብዘገይ ግን፥ በዚህ በጻፍሁልህ ትእዛዝ የሕያው እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን፥ የእውነት ዓምድና መሠረት በሆነችው በእግዚአብሔር ማደሪያ ቤት መኖር እንዴት እንደሚገባ እንድታውቅ ነው።
ፍርድ ከእግዚአብሔር ቤት ተነሥቶ የሚጀመርበት ጊዜ ደርሶአል፤ በቅድሚያም በእኛ የሚጀመር ከሆነ፥ ለእግዚአብሔር ወንጌል የማይታዘዙ መጨረሻቸው ምን ይሆን?