Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሕዝቅኤል 44:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በእስራኤል ልጆች መካከል ያለ የባዕድ ልጅ ሁሉ፥ ልቡ ያልተገረዘ ሥጋው ያልተገረዘ የባዕድ ልጅ ሁሉ ወደ መቅደሴ አይግባ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ በልቡና በሥጋው ያልተገረዘ ባዕድ በእስራኤላውያን መካከል የሚኖር ቢሆንም እንኳ ወደ መቅደሴ አይግባ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 ስለዚህ ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ሊታዘዙኝ ፈቃደኞች ያልሆኑት ያልተገረዙ ባዕዳን ሁሉ፥ በእስራኤል ሕዝብ መካከል የሚኖሩት እንኳ ቢሆኑ ወደተቀደሰው ስፍራዬ እንዲገቡ አይፈቀድላቸውም።”

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች መካ​ከል ከአ​ሉት ሁሉ በል​ቡና በሥ​ጋው ያል​ተ​ገ​ረዘ የባ​ዕድ ልጅ እን​ግዳ ሁሉ ወደ መቅ​ደሴ አይ​ግባ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በእስራኤል ልጆች መካከል ካሉት ሁሉ በልቡና በሥጋው ያልተገረዘ እንግዳ ሁሉ ወደ መቅደሴ አይግባ።

Ver Capítulo Copiar




ሕዝቅኤል 44:9
13 Referencias Cruzadas  

እኔም በተቀደሰው ተራራዬ በጽዮን የምቀመጥ ጌታ አምላካችሁ እንደሆንሁ ታውቃላችሁ፥ የዚያን ጊዜም ኢየሩሳሌም የተቀደሰች ትሆናለች፥ እንግዶችም ከእንግዲህ ወዲህ አያልፉባትም።


በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ያሉ ምንቸቶችም ሁሉ ለሠራዊት ጌታ የተቀደሱ ይሆናሉ። የሚሠውትም ሰዎች ሁሉ ይመጣሉ፥ በእነርሱም ውስጥ ይቀቅሉባቸዋል። በዚያም ቀን በሠራዊት ጌታ ቤት ከእንግዲህ ወዲያ ነጋዴ አይገኝም።


ምግቤን፥ ስብንና ደምን፥ በምታቀርቡበት ጊዜ ቤቴን እንዲያረክሱ በመቅደሴ ውስጥ እንዲሆኑ ያልተገረዘ ልብ፥ ያልተገረዘ ሥጋ ያላቸውን ባዕዳንን አግብታችኋል፥ በርኩሰታችሁም ሁሉ ቃል ኪዳኔን አፍርሰዋል።


ያመነና የተጠመቀ ይድናል፤ ያላመነ ግን ይፈረድበታል።


ምስክርነትህ እጅግ የታመነ ነው፥ አቤቱ፥ ለረጅም ዘመን፥ ለቤትህ ቅድስና ይገባል።


ክፉውን ግን እግዚአብሔር አለው፦ ለምን አንተ ሕጌን ትናገራለህ? ኪዳኔንም በአፍህ ለምን ትይዛለህ?


ለበጉም በሆነው በሕይወት መጽሐፍ ከተጻፉት በቀር፥ ጸያፍ ነገር ሁሉ ርኩሰትና ውሸትም የሚያደርግ ሁሉ ወደ እርሷ ከቶ አይገባም።


እኔም ደግሞ እነርሱን በመቃወም እሄዳለሁ፤ ወደ ጠላቶቻቸውም ምድር አመጣቸዋለሁ፤ ነገር ግን በዚያን ጊዜ ያልተገረዘው ልባቸው ቢዋረድ፥ የበደላቸውንም ቅጣት ቢቀበሉ፥


እንግዳ ሰውም በመካከላችሁ ቢቀመጥ ለጌታም ፋሲካን ሊያደርግ ቢፈልግ፥ እርሱና የእርሱ ወንዶች ሁሉ ይገረዙ ከዚያም ይቅረብ ያድርግም፤ እንደ አገሩ ተወላጅም ይሆናል፤ ያልተገረዘ ሁሉ ግን ከእርሱ አይብላ።


ምክንያቱም ከግብጽ ከወጣችሁ በኋላ በጉዞ ላይ በነበራችሁበት ጊዜ እህል ውሃ ይዘው አልተቀበሏችሁም፤ በመስጴጦምያ በምትገኘው በፐቶር ይኖር የነበረውን የቢዖርን ልጅ በለዓምም አንተን እንዲረግም በገንዘብ ገዝተውት ነበር።


ወደ ጌታ ተራራ ማን ይወጣል? በቅድስናውስ ስፍራ ማን ይቆማል?


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios