ዘካርያስ 11:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከእንግዲህ ወዲህ በምድር ላይ ለሚኖሩ አልራራም፥ ይላል ጌታ፤ እነሆም፥ ሰውን ሁሉ ለባልንጀራውና ለንጉሡ እጅ አሳልፌ እሰጣለሁ፤ ምድሪቱንም ይመታሉ፥ ከእጃቸውም አላስጥላቸውም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከእንግዲህ በምድሪቱ ለሚኖረው ሕዝብ አልራራምና” ይላል እግዚአብሔር፤ “ሰውን ሁሉ ለባልንጀራውና ለንጉሡ አሳልፌ እሰጣለሁ፤ እነርሱ ምድሪቱን ያስጨንቃሉ፤ እኔም ከእጃቸው አላድናቸውም።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “እኔም ከእንግዲህ ወዲህ በምድር ላይ ለሚኖር ለማንም ሰው ርኅራኄ አላደርግም፤ እኔ ራሴ እያንዳንዱን ሰው ለጐረቤቱና ለንጉሡ አሳልፌ እሰጣለሁ፤ እነርሱ ምድሪቱን ያጠፋሉ፤ እኔም ከእነርሱ እጅ አልታደጋቸውም።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእንግዲህ ወዲህ በምድር ላይ ለሚኖሩ አልራራም፥ ይላል እግዚአብሔር፣ እነሆም፥ ሰውን ሁሉ በባልንጀራውና በንጉሡ እጅ አሳልፌ እሰጣለሁ፣ ምድሪቱም ይመታሉ፥ ከእጃቸውም አላድናቸውም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእንግዲህ ወዲህ በምድር ላይ ለሚኖሩ አልራራም፥ ይላል እግዚአብሔር፥ እነሆም፥ ሰውን ሁሉ በባልንጀራውና በንጉሡ እጅ አሳልፌ እሰጣለሁ፥ ምድሪቱም ይመታሉ፥ ከእጃቸውም አላድናቸውም። |
ጫፎችዋ በደረቁ ጊዜ ይሰበራሉ፥ ሴቶችም መጥተው ያቃጥሉአቸዋል፤ የማያስተውል ሕዝብ ነውና ፈጣሪው አይራራለትም፤ ሠሪውም ምሕረት አያደርግለትም።
ዳግመኛም ፀነሰች ሴት ልጅም ወለደች። ጌታም እንዲህ አለው፦ “የእስራኤልን ቤት ፈጽሞ ይቅር እንድላቸው ከእንግዲህ ወዲህ ርኅራኄ የለኝምና ስምዋን ሎሩሃማ ብለህ ጥራት፤
ትበላለህ፥ ነገር ግን አትጠግብም፥ ባዶነትህም በመካከልህ ይሆናል፤ ትወስዳለህ፥ ነገር ግን ወደ ደህንነት አታመጣም፥ ወደ ደህንነት ያመጣኸውንም ለሰይፍ እሰጣለሁ።
የመንግሥታትንም ዙፋን እገለብጣለሁ፥ የአሕዛብ መንግሥታትን ኃይል አጠፋለሁ፤ ሰረገሎችንና ነጂዎቻቸውን እገለብጣለሁ፤ ፈረሶችንና ፈረሰኞቻቸው እያንዳንዱ በወንድሙ ሰይፍ ይወድቃሉ።
የገዙአቸው ያርዱአቸዋል፥ እንደ በደለኞች አይቆጠሩም፥ የሸጧቸውም፦ “ባለ ጠጋ ሆኛለሁ፤ ጌታ ይመስገን!” ይላሉ። እረኞቻቸው እንኳን አይራሩላቸውም።
ከነዚያ ወራት አስቀድሞ ለሰው ደሞዝ፥ ለእንስሳ ኪራይ አልነበረም፤ እኔም ሰውን ሁሉ በወንድሙ ላይ አስነሥቼ ስለ ነበር፥ በጠላቶቻቸው የተነሣ ወደዚያ ለሚገቡትና ለሚወጡት ሰላም አልነበራቸውም።
እነርሱ ግን “አስወግደው! አስወግደው! ስቀለው!” እያሉ ጮኹ። ጲላጦስም “ንጉሣችሁን ልስቀለውን?” አላቸው። የካህናት አለቆችም “ከቄሣር በቀር ሌላ ንጉሥ የለንም” ብለው መለሱለት
ለአሕዛብ እንዳንናገር በመከልከል እነርሱ እንዳይድኑ ያደርጋሉ፤ በዚህም ያለማቋረጥ የኃጢአታቸውን መስፈርያ ይሞላሉ፤ ነገር ግን በመጨረሻ የእግዚአብሔር ቁጣው ይመጣባቸዋል።
እኛስ እንዲህ ያለውን ታላቅ መዳን ቸል ብንለው፥ እንዴት እናመልጣለን? ይህ በጌታ በመጀመሪያ የተነገረ ነበርና፥ የሰሙትም ለእኛ ይህንኑ አረጋግጠውልናል።