ቲቶ 2:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህም ጸጋ፥ ኀጢአተኝነትንና ዓለማዊን ምኞት ክደን ራሳችንን በመቈጣጠርና በጽድቅ እግዚአብሔርንም በመምሰል በአሁኑ ዘመን እንድንኖር ይመክረናል፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህም ጸጋ በኀጢአት መኖርንና ዓለማዊ ምኞትን ክደን፣ በአሁኑ ዘመን ራሳችንን በመግዛትና በጽድቅ፣ በእውነተኛ መንፈሳዊ ሕይወት እንድንኖር ያስተምረናል፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህም ጸጋ ክሕደትንና ሥጋዊ ምኞትን በመተው ራስን በመቈጣጠር፥ በቀጥተኛነትና በመንፈሳዊነት በዚህ ዓለም እንድንኖር ያስተምረናል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይህም ጸጋ፥ ኀጢአተኝነትንና ዓለማዊን ምኞት ክደን፥ የተባረከውን ተስፋችንን እርሱም የታላቁን የአምላካችንንና የመድኃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ክብር መገለጥ እየጠበቅን፥ ራሳችንን በመግዛትና በጽድቅ እግዚአብሔርንም በመምሰል በአሁኑ ዘመን እንድንኖር ያስተምረናል፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይህም ጸጋ፥ ኃጢአተኝነትንና ዓለማዊን ምኞት ክደን፥ የተባረከውን ተስፋችንን እርሱም የታላቁን የአምላካችንንና የመድኃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ክብር መገለጥ እየጠበቅን፥ ራሳችንን በመግዛትና በጽድቅ እግዚአብሔርንም በመምሰል በአሁኑ ዘመን እንድንኖር ያስተምረናል፤ |
በሰው ልጅ ላይ ቃል የሚናገር ሁሉ ይሰረይለታል፤ በመንፈስ ቅዱስ ላይ ግን የሚናገር ሁሉ ግን በዚህ ዓለምም ቢሆን ወይም በሚመጣው አይሰረይለትም።
እርሱም ስለ ጽድቅና ራስን ስለ መግዛት ስለሚመጣውም ኩነኔ ሲነጋገር ሳለ፥ ፊልክስ ፈርቶ “አሁንስ ሂድ፥ በተመቸኝም ጊዜ ልኬ አስጠራሃለሁ፤” ብሎ መለሰለት።
መልካም፥ ደስ የሚያሰኝና ፍጹም የሆነውን የእግዚአብሔር ፈቃድ ምን እንደሆነ ለማወቅ በአእምሮአችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ።
ከሥጋችሁ ደካማነት የተነሣ እንደ ሰው አነጋገር እናገራለሁ። የሰውነታችሁን ክፍሎች ሕገ ወጥነትን ለሚያመጣ ለርኩሰትና ለሕገ ወጥነት ባርያዎች አድርጋችሁ እንዳቀረባችሁ፥ ስለዚህ አሁን የሰውነታችሁን ክፍሎች ቅድስና ለሚያመጣ ለጽድቅ ባርያዎች አድርጋችሁ አቅርቡ።
ትምክህታችን ይህ ነው፦ በዚህ ዓለም ይልቁንም በእናንተ ዘንድ፥ በእግዚአብሔር ጸጋ እንጂ በሥጋዊ ጥበብ ባልሆነ፥ በእግዚአብሔር ቅድስናና ቅንነት እንደኖርን፥ የሕሊናችን ምስክርነት ነው።
እንግዲህ ወዳጆች ሆይ! ይህ ተስፋ ቃል ስላለን፥ ሥጋንና መንፈስን ከሚያረክስ ነገር ሁሉ ራሳችንን እናንጻ፥ እግዚአብሔርን በመፍራት ቅድስናችንን ፍጹም እናድርግ።
በዚህም የዚህን ዓለም አኗኗር በመከተል፥ በማይታዘዙትም ልጆች ላይ አሁን ለሚሠራው መንፈስ አለቃ እንደ ሆነው፥ በአየር ላይ ሥልጣን እንዳለው አለቃ ፈቃድ እየታዘዛችሁ ትኖሩ ነበር።
በአሁኑ ዘመን ባለ ጠጎች የሆኑትን ሰዎች እንዳይታበዩ በሚያልፍም ባለጠግነት ላይ ሳይሆን እንድንደሰትበት ሁሉን አትረፍርፎ በሚሰጠን በሕያው እግዚአብሔር ላይ ተስፋ እንዲያደርጉ እዘዛቸው።
ዳሩ ግን ባለ ጠጎች ለመሆን የሚፈልጉ በፈተናና በወጥመድ፥ ሰዎችንም በጉስቁልናና በጥፋት ወስጥ በሚያሰጥሙአቸው ከንቱና ጎጂ በሆኑ በብዙ ምኞቶች ይወድቃሉ።
እኛ ደግሞ አስቀድመን የማናስተውል ነበርንና፤ የማንታዘዝ፥ የምንስት፥ ለምኞትና ለልዩ ልዩ ተድላ እንደ ባርያዎች የምንገዛ፥ በክፋትና በምቀኝነት ጊዜያችንን የምናሳልፍ፥ የምንጠላ፥ እርስ በርሳችንም የምንጠላላ ነበርን።
በእግዚአብሔር አብ ፊት ንጹሕና ያልረከሰ አምልኮ፥ “አባትና እናት የሞቱባቸውን ልጆች፥ እንዲሁም ባሎቻቸው የሞቱባቸውን ሴቶች በችግራቸው መርዳት፥ ራስንም ከዓለም ርኲሰት መጠበቅ ነው።”
እንግዲህ እነሆ፥ ጌታ እግዚአብሔርን የሚያመልኩትን ከፈተና እንዴት እንደሚያድናቸው፥ እንዲሁም በደለኞችን እንዴት በቅጣት ስር ለፍርድ ቀንም ጠብቆ እንደሚያቈያቸው ያውቃል።
እናንተ ግን ከእርሱ የተቀበላችሁት ቅባት በእናንተ ስለሚኖር፥ ማንም ሊያስተምራችሁ አያስፈልጋችሁም፤ የእርሱ ቅባት ስለ ሁሉም እንደሚያስተምራችሁ፥ እውነትም እንደሆነ ውሸትም እንዳልሆነ፥ እርሱ እንዳስተማራችሁ፥ በእርሱ ኑሩ።