ሮሜ 7:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በውስጣዊ ሰውነቴ በእግዚአብሔር ሕግ ደስ ይለኛልና፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በውስጤ በእግዚአብሔር ሕግ ሐሤት አደርጋለሁ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ውስጣዊ ሰውነቴ በእግዚአብሔር ሕግ ደስ ይለዋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በልቡናዬ ውስጥ ያለ የእግዚአብሔር ሕግ መልካም ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በውስጡ ሰውነቴ በእግዚአብሔር ሕግ ደስ ይለኛልና፥ |
ካህኑ ያያል፤ እነሆም፥ በሰውነታቸው ቆዳ ላይ ያለው ቋቁቻ ደብዘዝ ያለ ነጭ ቢሆን በቆዳ ላይ የሚወጣ ሽፍታ ነው፤ ከቆዳው ውስጥ ወጥቶአል፤ እርሱ ንጹሕ ነው።
ነገር ግን በስውር አይሁዳዊ የሆነ አይሁዳዊ ነው፤ መገረዝም በመንፈስ የሆነ የልብ መገረዝ ነው እንጂ በፊደል አይደለም፤ ምስጋናውም ከእግዚአብሔር ነው እንጂ ከሰው አይደለም።
ከዚያ ጊዜ በኋላ ከእስራኤል ቤት ጋር የምገባው ቃል ኪዳን ይህ ነው፥ ይላል ጌታ፤ ሕጌን በልቡናቸው አኖራለሁ፤ በልባቸውም እጽፈዋለሁ፤ እኔም አምላክ እሆንላቸዋለሁ፤ እነርሱም ሕዝብ ይሆኑልኛል።