167 ነፍሴ ምስክርህን ጠበቀች እጅግም ወደደችው።
167 ነፍሴ ምስክርነትህን ትጠብቃለች፤ እጅግ እወድደዋለሁና።
167 ትእዛዞችህን እጠብቃለሁ፤ በሙሉ ልቤም እወዳቸዋለሁ።
“ከነዚያ ወራት በኋላ ከእነርሱ ጋር የምገባው ኪዳን ይህ ነው፥ ይላል ጌታ፤ “በልባቸው ሕጌን አኖራለሁ፥ በልቡናቸውም እጽፈዋለሁ፤”
በውስጣዊ ሰውነቴ በእግዚአብሔር ሕግ ደስ ይለኛልና፥
በዚያን ጊዜ እንዲህ አልሁ፦ “እነሆ፥ መጣሁ፥ ስለ እኔ በመጽሐፍ ራስ ተጽፎአል፥
ትእዛዝህን እንደ ወደድሁ ተመልከት፥ አቤቱ፥ በምሕረትህ ሕያው አድርገኝ።
የልቤ ደስታ ነውና ምስክርህን ለዘለዓለም ወረስሁ።
አቤቱ፥ ሕግህን እንደምን እጅግ ወደድሁ! ቀኑን ሁሉ እርሱ ትዝታዬ ነው።
እጅግም በወደድኋቸው በትእዛዛትህ ደስ ይለኛል።