ሮሜ 7:23 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)23 ነገር ግን ከአእምሮዬ ሕግ ጋር የሚዋጋውንና በሰውነቴ ክፍሎች ባለ በኃጢአት ሕግ ምርኮኛ የሚያደርገኝ ሌላ ሕግ በሰውነቴ ክፍሎች አያለሁ። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም23 ነገር ግን በብልቶቼ ውስጥ ለሚሠራው የኀጢአት ሕግ እኔን እስረኛ በማድረግ፣ ከአእምሮዬ ሕግ ጋራ የሚዋጋ ሌላ ሕግ በብልቶቼ ውስጥ ሲሠራ አያለሁ። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም23 ይሁን እንጂ ከአእምሮዬ ሕግ ጋር እየተቃረነ በሰውነቴ ክፍሎች ውስጥ ለሚሠራው የኃጢአት ሕግ እስረኛ የሚያደርገኝ ሌላ የተፈጥሮ ዝንባሌ በሰውነቴ ክፍሎች ውስጥ መኖሩን አያለሁ። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)23 ነገር ግን በሰውነቴ ውስጥ ያለውን ሌላ የኀጢአት ሕግ እመለከታለሁ፤ በልቡናዬም ውስጥ ካለው ከእግዚአብሔር ሕግ ጋር ተሰልፈው ተዋጉ፤ በሰውነቴ ውስጥ ያለው ያ የኀጢአት ሕግም በረታና ወደ እርሱ ማረከኝ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)23 ነገር ግን በብልቶቼ ከአእምሮዬ ሕግ ጋር የሚዋጋውንና በብልቶቼ ባለ በኃጢአት ሕግ የሚማርከኝን ሌላ ሕግ አያለሁ። Ver Capítulo |