35 እርሷን ወድጃለሁና የትእዛዝህን መንገድ ምራኝ።
35 በርሷ ደስ ይለኛልና፣ በትእዛዝህ መንገድ ምራኝ።
35 ትእዛዞችህ ስለሚያስደስቱኝ እንድፈጽማቸው እርዳኝ።
ነፍሴን መለሳት፥ ስለ ስሙም በጽድቅ መንገድ መራኝ።
አቤቱ፥ መንገድህን አመልክተኝ፥ ፈለግህንም አስተምረኝ።
በጎ ፈቃዱን እንድትፈልጉና እንድታደርጉ ሁለቱንም በእናንተ ውስጥ የሚሠራ እግዚአብሔር ነውና።
የጥበብን መንገድ አስተማርሁህ፥ በቀናች ጎዳና መራሁህ።
ትእዛዛቱን እንድንጠብቅ፥ የእግዚአብሔር ፍቅር ይህ ነውና፤ ትእዛዛቱም ከባዶች አይደሉም።
በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል በፊቱ ደስ የሚያሰኘውን በእናንተ እያደረገ፥ ፈቃዱን ትፈጽሙ ዘንድ በመልካም ሥራ ሁሉ ፍጹማን ያድርጋችሁ፤ ለእርሱ እስከ ዘላለም ድረስ ክብር ይሁን፤ አሜን።
በውስጣዊ ሰውነቴ በእግዚአብሔር ሕግ ደስ ይለኛልና፥
እኔ በጽድቅ መንገድ እሄዳለሁ፥ በፍርድም ጎዳና መካከል፥
የድንጋጌዎችህን መንገድ እንዳስተውል አድርገኝ፥ ተኣምራትህንም አሰላስላለሁ።
በድንጋጌዎችህ ደስ ይለኛል፥ ቃልህንም አልረሳም።
ታዳጊህ፥ የእስራኤል ቅዱስ፥ ጌታ እንዲህ ይላል፦ እኔ የሚረባህን ነገር የማስተምርህ በምትሄድባትም መንገድ የምመራህ አምላክህ ጌታ ነኝ።
ብዙ ሕዝቦችም መጥተው እንዲህ ይላሉ፤ “ኑ፤ ወደ ጌታ ተራራ፤ ወደ ያዕቆብ አምላክ ቤት እንውጣ፤ እርሱ መንገዱን ያስተምረናል፤ በጎዳናውም እንሄዳለን።” ሕግ ከጽዮን፤ የእግዚአብሔር ቃል ከኢየሩሳሌም ይወጣልና።
የጻድቃን መንገድ ግን እንደ ንጋት ብርሃን ነው፥ ሙሉ ቀን እስኪሆንም ድረስ እየተጨመረ ይበራል።
መንገድዋ የደስታ መንገድ ነው፥ ጎዳናዋም ሁሉ ሰላም ነው።
ትእዛዛትህን መርጫለሁና እጅህ የሚያድነኝ ይሁን።
ልቤን ወደ ምስክርህ አዘንብል፥ ወደ ስስትም አይሁን።
ነገር ግን በጌታ ሕግ ደስ የሚለው፥ ሕጉንም በቀንና በሌሊት የሚያስብ።