ሮሜ 11:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንግዲህ የእግዚአብሔርን ቸርነትና ጭከና ተመልከት፤ ጭከናው በወደቁት ላይ ነው፤ በቸርነቱ ግን ጸንተህ ብትኖር የእግዚአብሔር ቸርነት በአንተ ላይ ነው፤ ያለዚያ አንተ ደግሞ ትቆረጣለህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንግዲህ የእግዚአብሔርን ቸርነትና ጭካኔ ተመልከት፤ ጭካኔውም በወደቁት ላይ ነው፤ ቸርነቱ ግን በቸርነቱ ውስጥ እስካለህ ድረስ ለአንተ ነው፤ አለዚያ ግን አንተም ትቈረጣለህ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንግዲህ የእግዚአብሔርን ቸርነትና አስፈሪነት ተመልከቱ፤ አስፈሪነቱን የሚያሳየው በወደቁት ላይ ሲሆን ቸርነቱን የሚያሳየው ግን ለእናንተ ነው፤ ይህንንም የሚያደርገው እርሱን በማመን ጸንታችሁ ብትኖሩ ነው፤ ባትጸኑ ግን እናንተም ተቈርጣችሁ ትወድቃላችሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንግዲህ የእግዚአብሔርን ርኅራኄውንና ጭካኔውን አስተውል፤ የወደቁትን ቀጣቸው፤ አንተን ግን ይቅር እንዳለህ ብትኖር ማረህ፤ ያለዚያ ግን አንተም ትቈረጣለህ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንግዲህ የእግዚአብሔርን ቸርነትና ጭከና ተመልከት፤ ጭከናው በወደቁት ላይ ነው፥ በቸርነቱ ግን ጸንተህ ብትኖር የእግዚአብሔር ቸርነት በአንተ ላይ ነው፤ ያለዚያ አንተ ደግሞ ትቆረጣለህ። |
ታያላችሁ፥ ልባችሁም ሐሤት ታደርጋለች፥ አጥንታችሁም እንደ ለምለም ሣር ትበቅላለች፤ የጌታም እጅ ለሚፈሩት ትታወቃለች፥ በጠላቶቹም ላይ ይቈጣል።
ጻድቁ ግን ከጽድቁ ቢመለስ፥ በደልንም ቢሠራ፥ ክፉ ሰው እንደሚያደርገው ርኩሰት ሁሉ ቢያደርግ፥ በሕይወት ይኖራልን? የሠራው ጽድቅ ሁሉ አይታሰብለትም፤ ታማኝ ባለመሆኑና በሠራው ኃጢአት በእነሱ ይሞታል።
ጻድቁ ደግሞ ከጽድቁ ተመልሶ ኃጢአት ከሠራ፥ እኔም በፊቱ ዕንቅፋትን አደርጋለሁ፥ እርሱም ይሞታል፤ አንተም አላስጠነቀቅኸውምና በኃጢአቱ ይሞታል፥ የጽድቁም ሥራ አይታሰብለትም፥ ደሙን ግን ከእጅህ እፈልጋለሁ።
ስለዚህ እኔ ደግሞ ወደ ፊት ለመታገስ ባልተቻለኝ ጊዜ፦ “ፈታኙ ምናልባት ፈትኖአቸዋል፤ ድካማችንም ከንቱ ሆኖአል፤” ብዬ በመፍራት እምነታችሁን ለማወቅ ጢሞቴዎስን ላክሁ።
ከእኛ ዘንድ ወጡ፥ ነገር ግን ከእኛ ወገን አልነበሩም፤ ከእኛ ወገንስ ቢሆኑ ኖሮ ከእኛ ጋር በኖሩ ነበር፤ ነገር ግን ሁሉ ከእኛ ወገን እንዳልሆኑ እንዲገለጥ ወጡ።
እንግዲህ ከየት እንደ ወደቅህ አስብ፤ ንስሓም ግባ፥ የቀደመውንም ሥራህን አድርግ፤ አለዚያ እመጣብሃለሁ ንስሓም ባትገባ መቅረዝህን ከስፍራው እወስዳለሁ።