ራእይ 9:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በእነዚህም መቅሠፍቶች ያልተገደሉት የቀሩቱ ሰዎች ስለ እጃቸው ሥራ ንስሓ አልገቡም፤ ለአጋንንትና ማየት ወይም መስማት ወይም መሄድ ለማይችሉ ከወርቅና ከብር ከናስም ከድንጋይም ከእንጨትም ለተሠሩ ለጣዖቶችም መስገድን አልተዉም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በእነዚህ መቅሠፍቶች ሳይገደሉ የቀሩት ሰዎች አሁንም ከእጃቸው ሥራ ንስሓ አልገቡም፤ አጋንንትን እንዲሁም ማየት ወይም መስማት ወይም መሄድ የማይችሉትን፣ ከወርቅ፣ ከብር፣ ከናስ፣ ከድንጋይና ከዕንጨት የተሠሩትን ጣዖቶች ማምለክ አልተዉም፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በእነዚህ መቅሠፍቶች ከሞት የተረፉት የሰው ዘር ከእጃቸው ሥራ ተመልሰው ንስሓ አልገቡም፤ አጋንንትንና ከወርቅ፥ ከብር፥ ከናስ፥ ከድንጋይና ከእንጨት የተሠሩ ማየት ወይም መስማት ወይም መሄድ የማይችሉትን ጣዖቶች ማምለክንም አልተዉም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በእነዚህም መቅሠፍቶች ያልተገደሉት የቀሩቱ ሰዎች ለአጋንንትና ያዩ ወይም ይሰሙ ወይም ይሄዱ ዘንድ ለማይችሉ ከወርቅና ከብር ከናስም ከድንጋይም ከእንጨትም ለተሠሩ ለጣዖቶች እንዳይሰግዱ ስለ እጃቸው ሥራ ንስሓ አልገቡም፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በእነዚህም መቅሠፍቶች ያልተገደሉት የቀሩቱ ሰዎች ለአጋንንትና ያዩ ወይም ይሰሙ ወይም ይሄዱ ዘንድ ለማይችሉ ከወርቅና ከብር ከናስም ከድንጋይም ከእንጨትም ለተሠሩ ለጣዖቶች እንዳይሰግዱ ስለ እጃቸው ሥራ ንስሐ አልገቡም፤ |
አናጢውም አንጥረኛውን፥ በመዶሻም የሚያሳሳውን በመስፍ ላይ የሚቀጠቅጠውን ያጽናናዋል፥ ስለ ብየዳ ሥራውም፦ “መልካም ነው” ይለዋል፤ እንዳይላቀቅም በችንካር ያጋጥመዋል።
ስለ ክፋታቸው ሁሉ ፍርዴን በእነርሱ ላይ እናገራለሁ፥ እኔን ትተውኛል፤ ለሌሎችም አማልክት ዕጣንን አጥነዋል፤ ለእጃቸውም ሥራዎች ሰግደዋልና።
እናንተም እንድትጠፉ በምድርም አሕዛብ ሁሉ መካከል መረገሚያና መሰደቢያ እንድትሆኑ፥ ለመቀመጥ በገባችሁባት በግብጽ ምድር ለሌሎች አማልክት አጥናችሁ በእጃችሁ ሥራ ለምን ታስቈጡኛላችሁ?
አቤቱ! ዓይንህ እውነትን የምትመለከት አይደለችምን? አንተ ቀሥፈሃቸዋል ነገር ግን አላዘኑም፥ ቀጥቅጠሃቸዋልም ነገር ግን ተግሣጽን ለመቀበል እንቢ አሉ፤ ፊታቸውን ከድንጋይ ይልቅ አጠንክረዋል፤ ለመመለስ እንቢ አሉ።
ሰው ሁሉ ቂላ ቂልና እውቀት የሌለው ሆኖአል፥ አንጥረኛም ሁሉ ከቀረጸው ምስል የተነሣ አፍሮአል፤ ቀልጦ የተሠራ ምስሉ ውሸት ነውና፥ እስትንፋስም የላቸውምና።
ስለዚህ ተከትለዋቸው ላመነዘሩባቸው ለሰይጣናት ከእንግዲህ ወዲህ መሥዋዕታቸውን አይሠዉም። ይህ ለእነርሱ ለልጅ ልጃቸው ለዘለዓለም ሥርዓት ይሁን።
ዮሐንስ በጽድቅ መንገድ ወደ እናንተ መጥቶ ነበር፥ አላመናችሁትም፤ ቀራጮችና ዘማውያን ግን አመኑት፤ በመጨረሻም ይህንን አይታችሁ እንኳ ልታምኑት ንስሐ አልገባችሁም።
እንግዲህ የእግዚአብሔር ዘመዶች ከሆንን፥ አምላክ በሰው ብልሃትና አሳብ የተቀረጸውን ወርቅ ወይም ብር ወይም ድንጋይ እንዲመስል እናስብ ዘንድ አይገባንም።
ይህም ጳውሎስ ‘በእጅ የተሠሩቱ አማልክት አይደሉም፤’ ብሎ፥ በኤፌሶን ብቻ ሳይሆን ከጥቂት ክፍል በቀር በእስያ ሁሉ ብዙ ሕዝብን እንደ አስረዳና እንደ አሳተ አይታችኋል፤ ሰምታችሁማል።
እንደገና ስመጣ በእናንተ ፊት አምላኬ ያዋርደኝ ይሆን እያልኩ፥ ከዚህ በፊት ስለ ሠሩት ኃጢአትና ስለ ፈጸሙትም ርኩሰት፥ ዝሙትና መዳራት ንስሓ ሳይገቡ ቀርተው እንዳላዝን እፈራለሁ።
እኔ ከሞትሁ በኋላ ፈጽማችሁ እንደምትረክሱ፥ ካዘዝኋችሁም መንገድ ዘወር እንደምትሉ ዐውቃለሁና። በጌታ ፊት ክፉ ድርጊት ስለምትፈጽሙ፥ እጆቻችሁ በሠሯቸውም ነገሮች እርሱን ስለምታስቆጡት በሚመጡት ዘመናት ጥፋት ይደርስባችኋል።”
መንፈስ ግን በግልጥ እንዲህ ይላል በኋለኞች ዘመናት አንዳንዶች የሚያስቱ መናፍስትንና የአጋንንትን ትምህርት ትኩረት በመስጠት እምነትን ይክዳሉ፤
ሌላም ታላቅና ድንቅ ምልክት በሰማይ አየሁ፤ የእግዚአብሔር ቁጣ በእነርሱ ስለሚፈጸም ኋለኛዎቹን ሰባት መቅሠፍቶች የያዙ ሰባት መላእክት ታዩ።