መዝሙር 94:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሕዛብንስ የሚገሥጸው፥ ለሰውም እውቀት የሚያስተምረው እርሱ አይቀጣምን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሕዝቦችን በተግሣጽ ወደ መንገድ የሚመልስ፣ ዕውቀትንስ ለሰው ልጆች የሚያስተምር አይቀጣምን? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሕዝቦችን የሚገሥጸው አይቀጣምን የሰውን ዘር የሚያስተምረው ዕውቀት የለውምን? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ይችን ትውልድ አርባ ዓመታት ተቈጥቻት ነበር፥ ሁልጊዜ ልባቸው ይስታል፥ እነርሱም መንገዴን አላወቁም” አልሁ። |
ጌታ በጽዮን ተራራና በኢየሩሳሌም ላይ የሚያደርገውን ሁሉ ከፈጸመ በኋላ፤ እንዲህ ይላል የአሦርን ንጉሥ ስለ ልቡ ትዕቢትና ስለ ንቀት አመለካከቱ እቀጣዋለሁ፤
ብዙ ሕዝቦችም መጥተው እንዲህ ይላሉ፤ “ኑ፤ ወደ ጌታ ተራራ፤ ወደ ያዕቆብ አምላክ ቤት እንውጣ፤ እርሱ መንገዱን ያስተምረናል፤ በጎዳናውም እንሄዳለን።” ሕግ ከጽዮን፤ የእግዚአብሔር ቃል ከኢየሩሳሌም ይወጣልና።
ያዕቆብን በልተውታልና፥ ውጠውታልምና፥ አጥፍተውታልምና፥ ማደሪያውንም አፍርሰዋልና በማያውቁህ አሕዛብ ስምህንም በማይጠሩ ወገኖች ላይ መዓትህን አውርድ።
ጌታ አምላኬ፥ ቅዱሴ ሆይ፥ አንተ ከጥንት ጀምሮ አልነበርህምን? እኛ አንሞትም፤ ጌታ ሆይ፥ ለፍርድ ወስነሃቸዋል፥ ዓለት ሆይ ለተግሣጽም መሠረትሃቸው።