ሰሎሞን ከሊባኖስ ዛፍ ጀምሮ በቤት ግንብ ላይ እስከሚበቅለው ሂሶጵ ድረስ ስለ ዛፎችና ስለ ተክሎች በምሳሌ እየመሰለ ተናግሮአል፤ እንዲሁም ስለ ልዩ ልዩ እንስሶች፥ ስለ ወፎች በሆዳቸው እየተሳቡ ስለሚሄዱ ፍጥረቶችና ስለ ዓሣዎችም አስተምሮአል።
መዝሙር 92:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዓይኔም ጠላቶቼን ቃኘች፥ ጆሮዬም በእኔ ላይ የተነሡትን ክፉዎች ሰማች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጻድቃን እንደ ዘንባባ ይንሰራፋሉ፤ እንደ ሊባኖስ ዝግባም ይንዠረገጋሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ደጋግ ሰዎች እንደ ዘንባባ ዛፍ ይለመልማሉ፤ እንደ ሊባኖስ ዛፍም ያድጋሉ። |
ሰሎሞን ከሊባኖስ ዛፍ ጀምሮ በቤት ግንብ ላይ እስከሚበቅለው ሂሶጵ ድረስ ስለ ዛፎችና ስለ ተክሎች በምሳሌ እየመሰለ ተናግሮአል፤ እንዲሁም ስለ ልዩ ልዩ እንስሶች፥ ስለ ወፎች በሆዳቸው እየተሳቡ ስለሚሄዱ ፍጥረቶችና ስለ ዓሣዎችም አስተምሮአል።
እርሱም በውኃ ፈሳሾች ዳር እንደ ተተከለ፥ ፍሬውን በየጊዜው እንደሚሰጥ፥ ቅጠሉም እንደማይረግፍ ዛፍ ይሆናል፥ የሚሠራውም ሁሉ ይከናወንለታል።
ሌላ እንዲቀመጥበት አይሠሩም፥ ሌላም እንዲበላው አይተከሉም፤ የሕዝቤ ዕድሜ እንደ ዛፍ ዕድሜ ይሆናልና፥ እኔም የመረጥኋቸው በእጃቸው ሥራ ረጅም ዘመን ደስ ይላቸዋል።
በውኃ አጠገብ እንደ ተተከለ፥ በወንዝም ዳር ሥሮቹን እንደሚዘረጋ፥ ሙቀትም በመጣ ጊዜ እንደማይፈራ፥ ቅጠሉም እንደሚለመልም፥ በድርቅ ዓመትም እንደማይሠጋ ፍሬውንም ከማፍራት እንደማያቋርጥ ዛፍ ይሆናል።”
“እኔ ግን ቁመቱ እንደ ዝግባ ቁመት፥ ብርታቱም እንደ ባሉጥ ዛፍ የነበረውን አሞራዊውን ከፊታቸው ደመሰስሁ፤ ፍሬውንም ከላዩ፥ ሥሩንም ከታቹ አጠፋሁ።
ወደፊትም ተዘርግቶ እንዳለው ሸለቆች፥ በወንዝ ዳር እንዳሉ አትክልቶች፥ ጌታ እንደ ተከለው ዓልሙን በውኃም ዳር እንዳሉ ዝግባዎች ተዘርግተዋል።