La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




መዝሙር 82:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

አቤቱ፥ ተነሥ፥ በምድር ላይ ፍረድ፥ አንተ አሕዛብን ሁሉ ትወርሳለህና።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

አምላክ ሆይ፤ ተነሥ፤ በምድር ላይ ፍረድ፣ ሕዝቦች ሁሉ ርስትህ ናቸውና።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

አምላክ ሆይ! ተነሥ! መንግሥታት ሁሉ ያንተ ስለ ሆኑ ለዓለም ፍርድን ስጥ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

አሦ​ርም ከእ​ነ​ርሱ ጋር ተባ​በረ፥ ለሎጥ ልጆ​ችም ረዳት ሆኑ​አ​ቸው።

Ver Capítulo



መዝሙር 82:8
14 Referencias Cruzadas  

አንተ ግን፥ አቤቱ፥ ለዘለዓለም ትኖራለህ፥ መታሰቢያህም ለልጅ ልጅ ነው።


ምላሳችንን እናበረታለን፥ ከንፈራችን የእኛ ነው፥ ጌታችን ማን ነው? የሚሉትን።


ለምነኝ፥ አሕዛብን ለርስትህ የምድርንም ዳርቻ ለግዛትህ እሰጥሃለሁ።


የምድር ዳርቻዎች ሁሉ ያስቡ፥ ወደ ጌታም ይመለሱ፥ የአሕዛብ ነገዶች ሁሉ በፊቱ ይሰግዳሉ።


ነፍሳችን በመሬት ላይ ተጐሳቁላለችና፥ ሆዳችንም ከምድር ጋር ተጣብቃለችና።


ጠላት ነፍሴን ያሳድዳት ያግኛትም፥ ሕይወቴንም በምድር ላይ ይርገጣት፥ ክብሬንም በትቢያ ላይ ያዋርዳት።


የምድር ትሑታንን ያድን ዘንድ እግዚአብሔር ለፍርድ በተነሣ ጊዜ።


የምድር ፈራጅ ሆይ፥ ተነሥ፥ ለትዕቢተኞች ፍዳቸውን ክፈላቸው።


ይመጣልና፥ በምድር ላይ ሊፈርድ ይመጣልና፥ እርሱም ዓለምን በጽድቅ አሕዛብንም በቅንነት ይፈርዳል።


የጌታ ክንድ ሆይ! ተነሥ፥ ተነሥ፥ ኃይልንም ልበስ፤ በቀድሞው ወራትና በጥንቱ ዘመን በነበረው ትውልድ እንደ ሆነው ተነሥ። ረዓብን የቈራረጥህ ዘንዶውንም የወጋህ አንተ አይደለህምን?


ታማኝ ሰው ከምድሪቱ ጠፍቶአል፥ በሰው መካከል ቅን የለም፤ ሁሉም ለደም ያደባሉ፥ እያንዳንዱም ወንድሙን በመረብ ያጠምዳል።


እኔ ግን ወደ ጌታ እመለከታለሁ፥ የመድኃኒቴን አምላክ እጠብቃለሁ፤ አምላኬ ይሰማኛል።


ስለዚህ “ጠብቁኝ” ይላል ጌታ፤ ለመበዝበዝ እስከምነሣበት ቀን ድረስ፥ ፍርዴ ሕዝቦችን ለመሰብሰብ፥ መንግሥታትንም ለማከማቸት ነው፥ ይህም መዓቴንና የቁጣዬን ትኩሳት ሁሉ ለማፍሰስ ነው፤ በቅንዓቴ እሳት ምድርም ሁሉ ትበላለችና።


ሰባተኛው መልአክ መለከቱን ነፋ፤ በሰማይም እንዲህ የሚሉ ታላላቅ ድምፆች ተሰሙ፦ “የዓለም መንግሥት የጌታችንና የመሢሑ ሆነች፤ ለዘለዓለምም እስከ ዘለዓለም ይነግሣል፤”