መዝሙር 47:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ ልዑል ግሩምም ነውና፥ በምድር ሁሉ ላይም ታላቅ ንጉሥ ነውና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሕዝቦችን ከእኛ በታች አደረገ፤ መንግሥታትንም ከእግራችን ሥር አስገዛልን። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱ ሕዝቦች ጸጥ ብለው እንዲገዙልንና መንግሥታትም በቊጥጥራችን ሥር እንዲሆኑ አደረገ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በተቀበሏት ጊዜ እግዚአብሔር በረከትዋን ያውቃል |
የአሕዛብ ንጉሥ ሆይ! በአሕዛብ ጥበበኞች ሁሉ መካከል በመንግሥታቸውም ሁሉ እንደ አንተ ያለ ስለ ሌለ፥ አንተን መፍራት ይገባልና አንተን የማይፈራ ማን ነው?
“በመንጋው ውስጥ ተባዕት እያለው ለጌታ ተስሎት እያለ ነውር ያለበትን የሚሠዋ ተንኮለኛ ሰው የተረገመ ነው። እኔ ታላቅ ንጉሥ ነኝና፥” ይላል የሠራዊት ጌታ፥ “ስሜም በሕዝቦች መካከል የተፈራ ነውና።”
እስራኤል ሆይ፥ ምስጉን ነህ፥ በጌታ የዳነ ሕዝብ እንደ አንተ ማን ነው? እርሱ የረድኤትህ ጋሻ፥ የከፍተኛነትህም ሰይፍ ነው። ጠላቶችህም ይገዙልሃል፥ አንተም ከፍታቸውን ትረግጣለህ።”
ጌታም ለአባቶቻቸው እንደ ማለላቸው በዙሪያቸው ካሉት አሳረፋቸው፤ ከጠላቶቻቸውም ሁሉ ማንም ሰው ሊቋቋማቸው አልቻለም፤ ጌታም ጠላቶቻቸውን ሁሉ በእጃቸው አሳልፎ ሰጣቸው።