መዝሙር 29:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጌታ ድምፅ በውኆች ላይ፥ የክብር አምላክ አንጐደጐደ፥ አምላክ በብዙ ውኆች ላይ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእግዚአብሔር ድምፅ በውሆች ላይ ነው፤ የክብር አምላክ አንጐደጐደ፤ እግዚአብሔር በታላላቅ ውሆች ላይ አንጐደጐደ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእግዚአብሔር ድምፅ በውቅያኖሶች ላይ ያስተጋባል፤ የክብር አምላክ እግዚአብሔር ከሚናወጠው ማዕበል በላይ ያንጐደጒዳል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አቤቱ፥ ነፍሴን ከሲኦል አወጣሃት፥ ወደ ጕድጓድም ከሚወርዱት ለይተህ አዳንኸኝ። |
እንዲህም ሆነ በሦስተኛው ቀን ማለዳ ነጎድጓድ፥ መብረቅና ከባድ ደመና እጅግም የበረታ የቀንደ መለከት ድምጽ በተራራው ላይ ሆነ፤ በሰፈሩ የነበሩት ሕዝብ ሁሉ ተንቀጠቀጡ።
በሰማይም ያለው የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ተከፈተ፤ የኪዳኑም ታቦት በቤተ በመቅደሱ ታየ፤ መብረቅና ድምፅም ነጐድጓድም የምድርም መናወጥ ታላቅም በረዶ ሆነ።
መብረቅና ድምጽም ነጎድጓድም ሆኑ፤ ትልቅም የምድር መናወጥ ሆነ፤ ሰው በምድር ከተፈጠረ ጀምሮ እንዲህ ያለ ታላቅ መናውጥ ከቶ አልነበረም፤ ነውጡ እጅግ ትልቅ ነበር።
የብዙ ሕዝብም ድምፅ፥ የብዙ ውሃዎችም ድምፅ፥ የብርቱም ነጐድጓድም ድምፅ የሚመስል ድምፅ እንዲህ ሲል ሰማሁ፤ “ሃሌ ሉያ! ሁሉን የሚገዛ ጌታ አምላካችን ነግሦአልና።
ከዙፋኑም መብረቅና ድምፅ ነጐድጓድም ይወጣል፤ በዙፋኑም ፊት ሰባት ችቦዎች ይቀጣጠሉ ነበር፤ እነርሱም ሰባቱ የእግዚአብሔር መናፍስት ናቸው።
ሳሙኤል የሚቃጠለውን መሥዋዕት በሚያሳርግበት ጊዜ፥ ፍልስጥኤማውያን እስራኤልን ለመውጋት ቀረቡ። ጌታ ግን በዚያ ዕለት በፍልስጥኤማውያን ላይ ከባድ የነጐድጓድ ድምፅ አንጐዳጐደባቸው፤ እነርሱም እጅግ ተሸበሩ፤ በእስራኤላውያን ፊት ድል ተመተውም ሸሹ።