መዝሙር 16:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ የርስቴ እድል ፈንታና ጽዋዬ ነው፥ ዕጣ ፈንታዬንም የምታጸና አንተ ነህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር የርስት ድርሻዬና ጽዋዬ ነው፤ ዕጣዬም በእጅህ ናት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ሆይ! ዕድል ፈንታዬና ጽዋዬ አንተ ነህ፤ ድርሻዬንም አስተማማኝ ታደርገዋለህ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰኰናዬ እንዳይናወጥ አረማመዴን በመንገድህ አጽና። |
ስለዚህም እርሱ ብዙዎችን ይወርሳል፥ ከኃያላንም ጋር ምርኮን ይከፋፈላል፤ ነፍሱን ለሞት አሳልፎ ሰጥቶአል፥ ከዓመፀኞችም ጋር ተቈጥሮአል፤ እርሱ ግን የብዙ ሰዎችን ኃጢአት ተሸከመ፥ ስለ ዓመፀኞችም ማለደ።
እናንተ የሮቤልና የጋድ ልጆች፥ ጌታ በእኛና በእናንተ መካከል ዮርዳኖስን ድንበር አድርጎአልና በጌታ ዘንድ ድርሻ የላችሁም ይሉአቸዋል።’ በዚህም ልጆቻችሁ ልጆቻችንን ጌታን እንዳይፈሩ ያደርጓቸዋል።
ነገር ግን በእኛና በእናንተ መካከል ከእኛም በኋላ በትውልዳችንና በትውልዳችሁ መካከል በሚቃጠል መሥዋዕትና በቁርባን በአንድነትም መሥዋዕታችን ጌታን እንድናገለግል፥ በሚመጣውም ዘመን ልጆቻችሁ ልጆቻንን፦ “በጌታ ዘንድ ድርሻ የላችሁም” እንዳይሉ ምስክር ይሆናል።’