መዝሙር 150:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ድምፁ መልካም በሆነ ጸናጽል አወድሱት፥ ድምፁ በሚሰማ ጸናጽል አወድሱት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ተርገብጋቢ ድምፅ ባለው ጸናጽል አመስግኑት፤ ድምፀ መልካም በሆነ ጸናጽል አመስግኑት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በጸናጽል ድምፅ አመስግኑት፤ ከፍተኛ ድምፅ ባለው ጸናጽል አመስግኑት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ድምፁ መልካም በሆነ ጸናጽል አመስግኑት፤ በጸናጽልና በእልልታ አመስግኑት። |
ዳዊትም በዜማ ዕቃ በመሰንቆና በበገና በጸናጽልም እንዲያዜሙ፥ ድምፃቸውንም በደስታ ከፍ እንዲያደርጉ መዘምራኑን ወንድሞቻቸውን እንዲሾሙ ለሌዋውያን አለቆች ተናገረ።
እንዲሁ እስራኤል ሁሉ ሆ እያሉ፥ ቀንደ መለከትና እምቢልታ እየነፉ፥ ጸናጽልና መሰንቆም በገናም እየመቱ፥ የጌታን የቃል ኪዳን ታቦት አመጡ።
አለቃው አሳፍ ነበረ፤ ከእርሱም ቀጥሎ መሰንቆና በገና ይጫወቱ የነበሩት ዘካርያስ፥ ይዒኤል፥ ሰሚራሞት፥ ይሒኤል፥ መቲትያ፥ ኤልያብ፥ በናያስ፥ ዖቤድ-ኤዶም፥ ይዒኤል ነበሩ፤ አሳፍም የጸናጽልን ድምፅ ያሰማ ነበረ።
ዳዊትና የሠራዊቱ አለቆችም ከአሳፍና ከኤማን ከኤዶታም ልጆች በመሰንቆና በበገና በጸናጽልም ትንቢት የሚናገሩትን ሰዎች ለማገልገል ለዩ፤ በአገልግሎታቸውም ሥራ ይሠሩ የነበሩት ሰዎች ቍጥር ይህ ነበረ።
እነዚህ ሁሉ በእግዚአብሔር ቤት በጸናጽልና በበገና በመሰንቆም እንዲዘምሩ፥ በእግዚአብሔርም ቤት እንዲያገለግሉ ከአባታቸው ትእዛዝ በታች ነበሩ፤ አሳፍም ኤዶታምም ኤማንም ከንጉሡ ትእዛዝ በታች ነበሩ።
መለከቱንም የሚነፉ መዘምራኑም በአንድነት ሆነው በአንድ ድምፅ ጌታን እያመሰገኑና እያከበሩ፦ “ጌታ መልካም ነውና፥ ጽኑ ፍቅሩም ለዘለዓለም ነውና” ጌታን አመስግኑ እያሉ ድምጻቸውን ወደ ላይ ከፍ አድርገው በመለከትና በጸናጽል በዜማም ዕቃ ሁሉ ጌታን ባመሰገኑ ጊዜ፥ ደመናው ቤቱን፥ የጌታን ቤት ሞላው።