እነሆ፥ ልጅ ይወለድልሃል፤ እርሱም ሰላም ያለው ሰው ይሆናል፤ በዙሪያው ካሉ ከጠላቶቹ ሁሉ አሳርፈዋለሁ፤ ስሙ ሰሎሞን ይባላልና፥ በዘመኑም ሰላምና ጸጥታን ለእስራኤል እሰጣለሁ።
መዝሙር 147:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በወሰንሽም ሰላምን አደረገ፥ የስንዴንም ስብ አጠገበሽ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በድንበርሽ ውስጥ ሰላም ያሰፍናል፤ ማለፊያ ስንዴም ያጠግብሻል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱ ወሰንሽን በሰላም ይጠብቃል፤ በመልካም ስንዴም ያጠግብሻል። |
እነሆ፥ ልጅ ይወለድልሃል፤ እርሱም ሰላም ያለው ሰው ይሆናል፤ በዙሪያው ካሉ ከጠላቶቹ ሁሉ አሳርፈዋለሁ፤ ስሙ ሰሎሞን ይባላልና፥ በዘመኑም ሰላምና ጸጥታን ለእስራኤል እሰጣለሁ።
ጌታ እንዲህ ይላል፦ እነሆም፥ ሰላምን እንደ ወንዝ፥ የአሕዛብንም ክብር እንደሚጐርፍ ፈሳሽ እመልስላታለሁ፤ ከዚያም ትጠባላችሁ፥ በጫንቃ ላይ ይሸከሙአችኋል በጉልበትም ላይ እያስቀመጡ ያቀማጥሏችኋል።
በወርቅና በብር አጌጥሽ፥ ልብስሽም ጥሩ በፍታ፥ ሐርና ወርቀዘቦ ነበር፥ የላመ ዱቄት፥ ማርና ዘይትም በላሽ፥ እጅግ በጣም ውብ ሆንሽ፥ ለንግሥትነትም በቃሽ።
በምድሪቱም ላይ ሰላምን እሰጣለሁ፥ ማንም ሳያስፈራራችሁ ያለ ስጋት ትተኛላችሁ፤ ክፉዎችንም አራዊት ከምድሪቱ አስወግዳለሁ፥ ሰይፍም በምድራችሁ ላይ አያልፍም።
አሁንም በዓይኔ ስቃያቸውን አይቻለሁና ከዚህ በኋላ ጨቋኝ አይመጣባቸውም፤ በቤቴ ዙሪያ እንደ ጠባቂ ጦር ሆኖ ከዘራፊዎች የሚጠብቅ እንዲሰፍር አደርጋለሁ።
የላሙንም ቅቤ፥ የመንጋውንም ወተት፥ ከሰቡት በጎችና ፍየሎች ጋር፥ የባሳንንም አውራ በጎች፥ ፍየሎችም፥ ከምርጥ ስንዴ ጋር በላህ፥ ከወይኑም ዘለላ የወይን ጠጅ ጠጣህ።”