15 መልእክቱን ወደ ምድር ይልካል፥ ቃሉም እጅግ ፈጥኖ ይሮጣል።
15 ትእዛዙን ወደ ምድር ይልካል፤ ቃሉም እጅግ በፍጥነት ይሮጣል።
15 ለምድር ትእዛዙን ያስተላልፋል፤ ቃሉም ወዲያው ይፈጸማል።
ለተግሣጽ ወይም ለምድሩ ወይም ለምሕረትም ቢሆን፥ ሰው በሚኖርበት ዓለም ላይ ያዘዘውን ሁሉ ያደርግ ዘንድ ፈቃዱ ወደ መራቸው ይዞራሉ።
በቀረውስ ወንድሞች ሆይ! በእናንተ መካከል እንደ ሆነው ሁሉ የጌታ ቃል ፈጥኖ እንዲስፋፋና እንዲከበር ስለ እኛ ጸልዩ፤
ኢየሱስም ለመቶ አለቃው “ሂድና እንደ እምነትህ ይሁንልህ፤” አለው። ብላቴናውም በዚያች ሰዓት ተፈወሰ።
ተናገረ፥ ዐውሎ ነፋስም ተነሣ፥ ሞገዶችንም አስነሣ።
ቃሉን ላከ ፈወሳቸውም፥ ከአዘቅትም አዳናቸው።
እንስሶችህ በውስጡ አደሩ፥ አቤቱ፥ በቸርነትህ ለድሆች አዘጋጀህ።
እርሱ ተናግሮአልና፥ ሆኑም፥ እርሱ አዘዘ፥ ጸኑም።
ጌታ ግን በባሕሩ ላይ ታላቅ ነፋስን አስነሣ፥ በባሕሩም ላይ ታላቅ ማዕበል ተነሣ፥ መርከቢቱም ልትሰበር ቀረበች።
ሕዝብንም ሆነ ሰውን በተመለከተ፥ ዝም ቢል የሚፈርድ ማን ነው? ፊቱንስ ቢሰውር የሚያየው ማን ነው?