“በአንተና በሴቲቱ መካከል፥ “በዘርህና በዘርዋም መካከል ጠላትነትን አደርጋለሁ፥ እርሱ ራስህን ይቀጠቅጣል፥ አንተም ሰኰናውን ትነድፋለህ።”
መዝሙር 110:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በአሕዛብ መካከል ይፈርዳል፥ ሬሳዎችንም ይከምራል፥ በሰፊ ምድር ላይ ራሶችን ይቀጠቅጣል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሕዝቦች መካከል ይፈርዳል፤ በየአገሩ ያሉትንም ራሶች ከስክሶ ሬሳ በሬሳ ያደርጋቸዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በአሕዛብ ላይ ይፈርዳል፤ የጦር ሜዳዎችንም ሬሳ በሬሳ ያደርጋል፤ በምድር ላይ ያሉትን ነገሥታት ሁሉ ይደመስሳል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የአሕዛብን ርስት ይሰጣቸው ዘንድ ለሕዝቡ የሥራውን ብርታት አሳየ። |
“በአንተና በሴቲቱ መካከል፥ “በዘርህና በዘርዋም መካከል ጠላትነትን አደርጋለሁ፥ እርሱ ራስህን ይቀጠቅጣል፥ አንተም ሰኰናውን ትነድፋለህ።”
እርሱ በሕዝቦች መካከል ይፈርዳል፤ የብዙ ሰዎችን አለመግባባት ያስወግዳል። እነርሱም ሰይፋቸውን ቀጥቅጠው ማረሻ ጦራቸውንም ማጭድ ያደርጋሉ። ሕዝብ በሕዝብ ላይ ሰይፍ አያነሣም፤ ጦርነትንም ከእንግዲህ አይማሩም።
ወጥተውም በእኔ ያመፁብኝን ሰዎች ሬሳቸውን ያያሉ፤ ትላቸው አይሞትምና፥ እሳታቸውም አይጠፋምና፤ ለሥጋ ለባሽም ሁሉ አስጸያፊ ነገር ይሆናሉ።
አንተ፥ ወታደሮችህና ከአንተም ጋር ያሉ ሕዝብ ሁሉ በእስራኤል ተራሮች ላይ ትወድቃላችሁ፤ ለሚናጠቁ ወፎች ሁሉና ለምድር አራዊትም መብል አድርጌ እሰጥሃለሁ።
በብዙዎች ሕዝቦች መካከል ይፈርዳል፥ በሩቅም ባሉ በብርቱዎች መንግሥታት ላይ ይበይናል፤ ሰይፋቸውን ወደ ማረሻ፥ ጦራቸውን ወደ ማጭድ ለመለወጥ ይቀጠቅጣሉ፤ መንግሥት በመንግሥት ላይ ሰይፍ አያነሣም፥ ከእንግዲህ ወዲህ ጦርነት አይማሩም።
የወይኑም መጥመቂያ ከከተማ ውጭ ተረገጠ፤ እስከ ፈረሶች ልጓም የሚደርስና እስከ አንድ ሺህ ስድስት መቶ ምዕራፍ ድረስ የሚርቅ ደም ከመጥመቂያው ወጣ።
ጌታ! እርሱን የሚቃወሙ ይደቅቃሉ፥ ከሰማይም ያንጐደጉድባቸዋል፥ ጌታ እስከ ምድር ዳርቻ ይፈርዳል፥ ለንጉሡም ኃይል ይሰጣል፥ የመሢሑንም ቀንድ ከፍ ከፍ ያደርጋል።”