መዝሙር 11:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በክፉዎች ላይ የእሳት ፍምንና ዲንን ያዘንባል የሚያቃጥል ነፋስም የጽዋቸው እድል ፈንታ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱ በክፉዎች ላይ የእሳት ፍምና ዲን ያዘንባል፤ የጽዋቸውም ዕጣ ፈንታ፣ የሚለበልብ ዐውሎ ነፋስ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በክፉዎች ላይ የእሳት ፍምንና ዲንን ያዘንባል፤ የሚጋረፍ ነፋስም የእነርሱ ዕድል ፈንታ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በምድር ላይ እንደ ተፈተነ፥ ሰባት ጊዜም እንደ ተጣራ ብር የእግዚአብሔር ቃል ንጹሕ ቃል ነው። |
ከዮሴፍ ገበታ ላይ እየተነሣ ለእያንዳንዳቸው ምግብ ሲቀርብ፥ የብንያም ድርሻ ከሌሎቹ አምስት ዕጥፍ ነበር። እነርሱም እንዲህ ባለ ሁኔታ አብረውት ተደሰቱ፤ እስኪረኩም ጠጡ።
ስለ ወገኑ የሚምዋገት አምላክሽ ጌታሽ እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ የሚያንገደግድን ጽዋ የቁጣዬንም ዋንጫ ከእጅሽ ወስጃለሁ፤ ደግመሽም ከእንግዲህ ወዲህ አትጠጪውም።
ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በመዓቴ በዐውሎ ነፋስ እሰነጣጥቀዋለሁ፥ በቁጣዬም ዶፍ ዝናብ፥ በመዓቴም ታላቅ የበረዶ ድንጋይ ሊያጠፋው ይወርዳል።
በቸነፈርና በደም እፈርድበታለሁ፤ ዶፍና የበረዶ ድንጋይ፥ እሳትና ዲን በእርሱና በወታደሮቹ ከእርሱም ጋር ባሉት ብዙ ሕዝቦች ላይ አዘንባለሁ።
በክብር ፈንታ እፍረት ሞልቶብሃል፤ አንተ ደግሞ ጠጣ፥ እንዳልተገረዘም ተቆጠር፤ የጌታ የቀኙ ጽዋ በአንተ ላይ ይመለስብሃል፥ እፍረትም በክብርህ ላይ ይሆናል።
ሕልቃና መሥዋዕት የሚሠዋበት ወቅት በደረሰ ጊዜ ሁሉ፥ ለሚስቱ ለጵኒና እንዲሁም ለወንዶችና ለሴቶች ልጆችዋ ሁሉ ድርሻቸውን ይሰጣቸው ነበር።