መንፈስህን ትልካለህ ይፈጠራሉም፥ የምድርንም ፊት ታድሳለህ።
መንፈስህን ስትልክ፣ እነርሱ ይፈጠራሉ፤ የምድርንም ገጽ ታድሳለህ።
እስትንፋስ ስትሰጣቸው ግን ይፈጠራሉ፤ ለምድርም አዲስ ሕይወት ትሰጣለህ።
ምድራቸው በንጉሦቻቸው ቤቶች ጓጕንቸሮችን አወጣች።
የሕያዋን ሁሉ ነፍስ የሰውም ሁሉ እስትንፋስ በእጁ ናት።
በመንፈሱ ሰማያት ውበትን አገኙ፥ እጁም የሚሸሸውን እባብ ወጋች።
የእግዚአብሔር መንፈስ ፈጠረኝ፥ ሁሉንም የሚችል የአምላክ እስትንፋስ ሕይወትን ሰጠኝ።
በጌታ ቃል ሰማዮች ጸኑ፥ በአፉም እስትንፋስ ሠራዊታቸው ተፈጠረ፥
እነሆ፥ አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር እፈጥራለሁ፤ የቀደሙትም አይታሰቡም፥ ትውስታቸውም አይኖርም።
እኔ የምሠራቸው አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር ከፊቴ ጸንተው እንደሚኖሩ፥ እንዲሁ ዘራችሁና ስማችሁ ጸንተው ይኖራሉ፥ ይላል ጌታ።
ጌታ እግዚአብሔር ለእነዚህ አጥንቶች እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ በእናንተ ላይ እስትንፋስ አገባባችኋለሁ በሕይወትም ትኖራላላችሁ።
ጅማትንም አደርግላችኋለሁ፥ ሥጋንም አወጣባችኋለሁ ቆዳ አለብሳችኋለሁ፥ በውስጣችሁ እስትንፋስ አገባባችኋለሁ፥ በሕይወትም ትኖራላችሁ፤ እኔም ጌታ እንደሆንሁ ታውቃላችሁ።
እንዲህም አለኝ፦ “ትንቢት ተናገር፥ ለነፋስ ትንቢት ተናገር የሰው ልጅ ሆይ፥ ነፋሱንም እንዲህ በለው፦ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ነፋስ ሆይ፥ ከአራቱ ነፋሳት ዘንድ ና፥ በሕይወት እንዲኖሩ በእነዚህ በተገደሉት ላይ እፍ በልባቸው።’”
እናንተ በበደላችሁና በኀጢአታችሁ ምክንያት ሙታን ነበራችሁ፤
እኛ በጽድቅ በሠራናቸው ሥራዎች ሳይሆን እንደ ምሕረቱ መጠን ለአዲስ ልደት በሚሆነው መታጠብና በመንፈስ ቅዱስ በመታደስ እኛን አዳነን፤
በዙፋንም የተቀመጠው “እነሆ ሁሉን አዲስ አደርጋለሁ፤” አለ። እኔንም “እነዚህ ቃሎች የታመኑና እውነተኛዎች ናቸውና ጻፍ፤” አለኝ።