ምሳሌ 21:29 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኀጥእ ፊቱን ያጠነክራል፥ ቅን ሰው ግን መንገዱን ያጸናል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ክፉ ሰው በዐጕል ድፍረት ይቀርባል፤ ቅን ሰው ግን አደራረጉን ያስተውላል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ክፉ ሰው “አልተሳሳትኩም” በማለት በግትርነት ይጸናል፤ እውነተኛ ሰው ግን ስለ ራሱ ጠባይ በጥንቃቄ ያስባል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኃጥእ ሰው ያለ ኀፍረት ፊት ለፊት ይቃወማል፤ ቅን ሰው ግን መንገዱን ይረዳል። |
አቤቱ! ዓይንህ እውነትን የምትመለከት አይደለችምን? አንተ ቀሥፈሃቸዋል ነገር ግን አላዘኑም፥ ቀጥቅጠሃቸዋልም ነገር ግን ተግሣጽን ለመቀበል እንቢ አሉ፤ ፊታቸውን ከድንጋይ ይልቅ አጠንክረዋል፤ ለመመለስ እንቢ አሉ።
አስጸያፊ ነገርን ስለ ሠሩ አፍረዋልን? ምንም አላፈሩም፥ እፍረትንም አላወቁም፤ ስለዚህ ከሚወድቁ ጋር ይወድቃሉ፤ በጐበኘኋቸው ጊዜ ይዋረዳሉ፥ ይላል ጌታ።”