59 ስለ መንገዶችህ አሰብሁ፥ እግሬንም ወደ ምስክሮችህ መለስሁ።
59 መንገዴን ቃኘሁ፤ አካሄዴንም ወደ ምስክርህ አቀናሁ።
59 አካሄዴን መርምሬ የተረዳሁት ስለ ሆነ ሥርዓትህን ለመከተል ቃል እገባለሁ።
በእምነት እንደምትኖሩ ለማወቅ ራሳችሁን መርምሩ፤ ራሳችሁን ፈትኑ፤ ወይስ ምናልባት የማትበቁ ካልሆናችሁ በቀር፥ ኢየሱስ ክርስቶስ በእናንተ ውስጥ እንዳለ አታውቁም ኖሯል?
የሠራውን በደል ሁሉ አይቶ ተመልሶአልና በእርግጥ በሕይወት ይኖራል እንጂ አይሞትም።
ኖን። መንገዳችንን እንመርምርና እንፈትን፥ ወደ እግዚአብሔርም እንመለስ።
እንደገና ስመጣ በእናንተ ፊት አምላኬ ያዋርደኝ ይሆን እያልኩ፥ ከዚህ በፊት ስለ ሠሩት ኃጢአትና ስለ ፈጸሙትም ርኩሰት፥ ዝሙትና መዳራት ንስሓ ሳይገቡ ቀርተው እንዳላዝን እፈራለሁ።
የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ ልባችሁን በመንገዳችሁ ላይ አድርጉ።
አሁንም የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ ልባችሁን በመንገዳችሁ ላይ አድርጉ።
ስለዚህ የእስራኤል ቤት ሆይ፥ እያንዳንዱን ሰው እንደ መንገዱ እፈርዳለሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር። ተመለሱ፥ ኃጢአትም ዕንቅፋት እንዳይሆንባችሁ ከኃጢአታችሁ ሁሉ ተመለሱ።
ልባችሁን እንጂ ልብሳችሁን አትቅደዱ፥ ጌታ አምላካችሁም ቸርና መሐሪ፥ ቁጣው የዘገየ፥ ጽኑ ፍቅሩ የበዛ፥ ለክፋትም የተጸጸተ ነውና ወደ እርሱ ተመለሱ።
ኃጢአተኛውም ከኃጢአቱ ተመልሶ ፍርድንና ቅን ነገርን ቢያደርግ በእነርሱ በሕይወት ይኖርበታል።
እርሷም በሰማች ጊዜ ፈጥና ተነሣች፥ ወደ እርሱም መጣች፤