ምሳሌ 1:31 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ የመንገዳቸውን ፍሬ ይበላሉ፥ የገዛ ራሳቸውን ምክር ይጠግባሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የመንገዳቸውን ፍሬ ይበላሉ፤ የዕቅዳቸውንም ውጤት ይጠግባሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ የሚገባችሁን ቅጣት ትቀበላላችሁ፤ የተንኰላችሁንም ውጤት ታገኛላችሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለዚህ የሥራቸውን ፍሬ ይበላሉ፥ በራሳቸውም ኀጢአት ይጠግባሉ። |
እኔ ደግሞ የተሳለቀባቸውን እመርጣለሁ፥ የፈሩትንም ነገር አመጣባቸዋለሁ። ምክንያቱም በፊቴ ክፉ ነገርን አድርገዋል፥ ያልወደድሁትንም መርጠው በጠራኋቸው ጊዜ አልመለሱልኝም፤ በተናገርሁም ጊዜ አልሰሙኝም።
ትንቢት የሚናገሩላቸውም ሰዎች ከራብና ከሰይፍ የተነሣ በኢየሩሳሌም አደባባይ ይጣላሉ፤እነርሱንና ሚስቶቻቸውን ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውንም የሚቀብራቸው አይገኝም፤ ክፋታቸውንም በእነርሱ ላይ አወርድባቸዋለሁ።
ክፋትሽ ይቀጣሻል ክህደትሽ ይገሥጽሻል፤ ጌታን አምላክሽን መተውሽ ምን ያኽል ክፉና መራራ ነገር እንደሆነ እወቂም፥ ተመልከቺም፤ እኔን መፍራት በአንቺ ውስጥ የለም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።