Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ምሳሌ 8:36 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

36 እኔን ያጣ ግን ራሱን ይጐዳል፥ የሚጠሉኝ ሁሉ ሞትን ይወድዳሉ።”

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

36 የሚያጣኝ ሁሉ ግን ራሱ ይጐዳል፤ የሚጠሉኝም ሁሉ ሞትን ይወድዳሉ።”

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

36 እኔን ያጣ ራሱን ይጐዳል፤ እኔን የሚጠላም ሞትን ይወዳል።”

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

36 በእኔ ላይ በደልን የሚፈጽሙ ራሳቸውን ይበድላሉ፤ የሚጠሉኝም ሞትን ይወድዳሉ።

Ver Capítulo Copiar




ምሳሌ 8:36
20 Referencias Cruzadas  

ኃጢአት ብትሠራ ምን ትጐዳዋለህ? መተላለፍህስ ቢበዛ ምን ታደርገዋለህ?


ስለዚህ የመንገዳቸውን ፍሬ ይበላሉ፥ የገዛ ራሳቸውን ምክር ይጠግባሉ።


አላዋቂዎችን ከጥበብ መራቅ ይገድላቸዋልና፥ ሞኞችንም ቸልተኛ መሆን ያጠፋቸዋልና።


ተግሣጽን የሚወድድ እውቀትን ይወድዳል፥ እርማትን የሚጠላ ግን ሞኝ ነው።


ተግሣጽን ቸል የሚል የራሱን ነፍስ ይንቃል፥ ዘለፋን የሚሰማ ግን አእምሮ ያገኛል።


የንጉሥ ቁጣ እንደ አንበሳ ግሣት ነው፥ የሚያስቈጣውም ሰው የራሱን ነፍስ ይበድላል።


በሐሰተኛ ምላስ መዝገብ ማከማቸት የሚበንን ጉም ነው፥ ይህን የሚፈልጉ ሞትን ይፈልጋሉ።


የፊታቸው ገጽታ ይመሰክርባቸዋል፤ ኀጢአታቸውን እንደ ሰዶም በይፋ ይናገራሉ፤ አይደብቁትምም፤ ጥፋትን በራሳቸው ላይ ስላመጡ ወዮላቸው!


ለባቢሎን ንጉሥ ማገልገልን እንቢ ስለሚል ሕዝብ ጌታ እንደ ተናገረው፥ አንተና ሕዝብህ በሰይፍና በራብ በቸነፈርም ለምን ትሞታላችሁ?


የበደላችሁትን በደል ሁሉ ከእናንተ ጣሉ፥ አዲስ ልብና አዲስ መንፈስም ለእናንተ አድርጉ፥ የእስራኤል ቤት ሆይ፥ ለምን ትሞታላችሁ?


በሕያውነቴ እምላለሁ ኃጢአተኛው ሰው ከመንገዱ ተመልሶ በሕይወት እንዲኖር እንጂ ኃጢአተኛው እንዲሞት አልፈቅድም፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ የእስራኤል ቤት ሆይ ተመለሱ፥ ከክፉ መንገዳችሁ ተመለሱ፤ ስለ ምንስ ትሞታላችሁ? በላቸው።


ጳውሎስና በርናባስም ገልጠው “የእግዚአብሔር ቃል አስቀድሞ ለእናንተ ይነገር ዘንድ ያስፈልጋል፤ ከገፋችሁትና የዘለዓለም ሕይወት እንዳይገባችሁ በራሳችሁ ከፈረዳችሁ ግን፥ እነሆ፥ ወደ አሕዛብ ዘወር እንላለን።


ጳውሎስ ግን በታላቅ ድምፅ “ሁላችን ከዚህ አለንና በራስህ ክፉ ነገር አታድርግ፤” ብሎ ጮኸ።


ጌታን የማይወድ ቢኖር የተረገመ ይሁን። ጌታችን ሆይ! ና!


እንግዲህ የእግዚአብሔርን ልጅ የረገጠ፥ የተቀደሰበትን ያንን የኪዳኑን ደም እንደ ርኩስ ነገር የቆጠረ፥ የጸጋውንም መንፈስ ያስቆጣ፥ ቅጣቱ እጅግ የከፋ እንዴት የማይሆን ይመስላችኋል?


እኛስ እንዲህ ያለውን ታላቅ መዳን ቸል ብንለው፥ እንዴት እናመልጣለን? ይህ በጌታ በመጀመሪያ የተነገረ ነበርና፥ የሰሙትም ለእኛ ይህንኑ አረጋግጠውልናል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos