ምሳሌ 14:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)14 ልቡን ከጽድቅ የሚመልስ ሰው ከመንገዱ ፍሬ ይጠግባል፥ ጻድቅም ሰው ደግሞ በራሱ። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም14 ልባቸውን ከጽድቅ የሚመልሱ የእጃቸውን ሙሉ ዋጋ ይቀበላሉ፤ ደግ ሰውም ወሮታውን ያገኛል። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም14 ከሐዲዎች ሰዎች የክፉ ሥራቸውን ዋጋ ይቀበላሉ፤ ደጋግ ሰዎች ግን የመልካም ሥራቸውን ዋጋ ያገኛሉ። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)14 ልበ ትዕቢተኛ ከራሱ መንገድ ይጠግባል። ደግ ሰውም ከራሱ ዐሳብ ይጠግባል። Ver Capítulo |
ጠቢብ ብትሆን ለራስህ ጠቢብ ትሆናለህ፥ ፌዘኛም ብትሆን ፌዘኛነትህን ለብቻህ ትሸከማለህ። (የሚቀጥለው ከግሪክ የተጨመረ ነው።) ልጄ ለራስህ አዋቂ ብትሆን ለባልንጀራህም አዋቂ ትሆናለህ፥ ለራስህ ክፉ ብትሆን ግን ክፋትን ለብቻህ ትሸከማለህ። ሐሰትን የሚያዘጋጅ ሰው ነፋሳትን እንደሚገዛ ነው፥ የሚበርር ወፍንም እንደሚከተል ይመስላል። የወይኑ ቦታ መንገዱን ረስቷልና፥ የሚሠማራባትን መንገድ እንዲስት አድርጓልና፥ ወደ ምድረ በዳ ይሄዳል፥ ለጥም ወደ ተሠራች አገር ይሄዳል፥ የማያፈራ የማይጠቅም ገንዘብንም በእጁ ይሰበስባል።