ደግሞም በጌታ አምሎት በነበረው በንጉሡ በናቡከደናፆር ላይ ዓመፀ፤ ወደ እስራኤልም አምላክ ወደ ጌታ እንዳይመለስ አንገቱን አደነደነ ልቡንም አጠነከረ።
ዘኍል 30:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሴትም ደግሞ በአባትዋ ቤት ሳለች በብላቴንነትዋ ጊዜ ለጌታ ስእለት ብትሳል፥ ወይም ራስዋን በመሐላ ብታስር፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “በአባቷ ቤት የምትኖር ሴት ልጅ ለእግዚአብሔር ስእለት ብትሳል ወይም አንድ ነገር ለማድረግ በመሐላ ራሷን ግዴታ ውስጥ ብታስገባ፣ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ገና በአባትዋ ቤት የምትኖር ልጃገረድ ለእግዚአብሔር አንድ ነገር ለመስጠት ብትሳል፥ ወይም ከአንድ ነገር ራስዋን ለመከልከል ቃል ብትገባ፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሴትም ደግሞ ለእግዚአብሔር ስእለት ብትሳል፥ እርስዋም በአባቷ ቤት ሳለች በብላቴንነቷ ጊዜ ራስዋን ብትለይ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሴትም ደግሞ ለእግዚአብሔር ስእለት ብትሳል፥ እርስዋም በአባትዋ ቤት ሳለች በብላቴንነትዋ ጊዜ ራስዋን በመሐላ ብታስር፥ |
ደግሞም በጌታ አምሎት በነበረው በንጉሡ በናቡከደናፆር ላይ ዓመፀ፤ ወደ እስራኤልም አምላክ ወደ ጌታ እንዳይመለስ አንገቱን አደነደነ ልቡንም አጠነከረ።
“ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ለእነርሱ ተናገር፦ ማናቸውም ሰው ሰውን ለጌታ ሊሰጥ ቢሳል፥ አንተ እንደምትገምተው መጠን ስለ ሰው ተመጣጣኝ የሆነውን ዋጋ ይስጥ።
አባትዋም ራስዋን ያሰረችበትን መሐላ ስእለትዋንም ቢሰማ፥ አባትዋም ዝም ቢላት፥ ስእለትዋ ሁሉ ይጸናል፥ ራስዋንም ያሰረችበት መሐላ ሁሉ ይጸናል።
ባያትም ጊዜ ልብሱን በመቅደድ፥ “ወይኔ ልጄ ጉድ አደረግሽኝ ጭንቅም ላይ ጣልሺኝ፤ ማስቀረት የማልችለውን ስእለት ለጌታ ተስያለሁና” ብሎ በኀዘን ጮኸ።
እንዲህም ብላ ስእለት ተሳለች፤ “የሠራዊት ጌታ ሆይ፤ የአገልጋይህን መዋረድ ተመልክተህ ብታስበኝ፥ ለአገልጋይህም ወንድ ልጅ ብትሰጣት፥ በሕይወት ዘመኑ ሁሉ ለጌታ እሰጠዋለሁ፤ ምላጭም በራሱ ላይ አያርፍም።”