በአምላካችን ፊት ራሳችንን ዝቅ እንድናደርግ፥ ከእርሱም የቀናውን መንገድ ለእኛና ለልጆቻችን ለንብረታችንም ሁሉ እንድንለምን በዚያ በአኅዋ ወንዝ አጠገብ ጾም አወጅሁ።
ዘኍል 30:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ስእለትዋን ሁሉ ራስዋንም የሚያዋርደውን መሐላ ሁሉ ባልዋ ያጸናዋል፥ ባልዋም ከንቱ ያደርገዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የትኛውንም ስእለቷን ወይም ራሷን ለመከላከል በመሐላ የታሰረችበትን ሁሉ ባሏ ሊያጸናው ወይም ሊያፈርሰው ይችላል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ባልዋ ማንኛውንም ስእለት ሆነ መሐላ የመፍቀድ ወይም የመቃወም መብት አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ስእለቷን ሁሉ፥ ነፍስዋንም የሚያዋርደውን የመሐላ ማሰሪያ ሁሉ ባልዋ ያጸናዋል፤ ወይም ባልዋ ይከለክለዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስእለትዋን ሁሉ ነፍስዋንም የሚያዋርደውን መሐላ ሁሉ ባልዋ ያጸናዋል፥ ባልዋም ከንቱ ያደርገዋል። |
በአምላካችን ፊት ራሳችንን ዝቅ እንድናደርግ፥ ከእርሱም የቀናውን መንገድ ለእኛና ለልጆቻችን ለንብረታችንም ሁሉ እንድንለምን በዚያ በአኅዋ ወንዝ አጠገብ ጾም አወጅሁ።
እኔ የመረጥሁት ጾም ይህ ነው? ሰውስ ነፍሱን የሚያዋርደው እንደዚህ ባለ ቀን ነው? በውኑ ራሱን እንደ እንግጫ ዝቅ እንዲያደርግ፥ ማቅንና አመድንም በበታቹ እንዲያነጥፍ ነው? በውኑ ይህን ጾም፥ በጌታ ዘንድ የተወደደ ቀን ብለህ ትጠራዋለህ?
“ይህም የዘለዓለም ሥርዓት ይሁንላችሁ፤ በሰባተኛው ወር ከወሩም በአስረኛው ቀን ራሳችሁን አዋርዱ፥ የአገሩም ተወላጅ ሆነ በእናንተ መካከል የተቀመጠም እንግዳ ሥራን ሁሉ አትሥሩበት፤
“በዚህ በሰባተኛው ወር አሥረኛው ቀን የማስተስረያ ቀን ነው፤ የተቀደሰ ጉባኤ ይሁንላችሁ፤ ራሳችሁን አዋርዱ፥ ለጌታም በእሳት የሚቀርበውን ቁርባን አቅርቡ።
ባልዋ ግን በሰማበት ቀን ከንቱ ቢያደርገው፥ ስለ ስእለትዋ ወይም ራስዋን ስላሰረችበት መሐላ በአንደበትዋ የተናገረችው ማናቸውም ነገር አይጸናም፤ ባልዋ ከንቱ አድርጎታል፤ ጌታም ይቅር ይላታል።
ለጸሎት ለመትጋት ተስማምታችሁ ለተወሰነ ጊዜ ካልሆነ በቀር፥ እርስ በርሳችሁ አትከላከሉ፤ እንዲሁም ራሳችሁን ስለ አለመግዛት ሰይጣን እንዳይፈታተናችሁ አብራችሁ ሁኑ።