Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘኍል 30:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 “ስእ​ለ​ቷን ሁሉ፥ ነፍ​ስ​ዋ​ንም የሚ​ያ​ዋ​ር​ደ​ውን የመ​ሐላ ማሰ​ሪያ ሁሉ ባልዋ ያጸ​ና​ዋል፤ ወይም ባልዋ ይከ​ለ​ክ​ለ​ዋል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 የትኛውንም ስእለቷን ወይም ራሷን ለመከላከል በመሐላ የታሰረችበትን ሁሉ ባሏ ሊያጸናው ወይም ሊያፈርሰው ይችላል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 “ስእለትዋን ሁሉ ራስዋንም የሚያዋርደውን መሐላ ሁሉ ባልዋ ያጸናዋል፥ ባልዋም ከንቱ ያደርገዋል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ባልዋ ማንኛውንም ስእለት ሆነ መሐላ የመፍቀድ ወይም የመቃወም መብት አለው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 ስእለትዋን ሁሉ ነፍስዋንም የሚያዋርደውን መሐላ ሁሉ ባልዋ ያጸናዋል፥ ባልዋም ከንቱ ያደርገዋል።

Ver Capítulo Copiar




ዘኍል 30:13
13 Referencias Cruzadas  

ነገር ግን የወ​ንድ ሁሉ ራሱ ክር​ስ​ቶስ፥ የሴ​ትም ራስዋ ወንድ፤ የክ​ር​ስ​ቶ​ስም ራሱ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆነ ልታ​ውቁ እወ​ድ​ዳ​ለሁ።


ወንድ ስለ ሴት አል​ተ​ፈ​ጠ​ረም፤ ሴት ስለ ወንድ ተፈ​ጠ​ረች እንጂ።


እኔ ይህን ጾም የመ​ረ​ጥሁ አይ​ደ​ለ​ሁም፤ እን​ደ​ዚ​ችም ባለች ቀን ሰው ራሱን ቢያ​ሳ​ዝን፥ አን​ገ​ቱ​ንም እንደ ቀለ​በት ቢያ​ቀ​ጥን፥ ማቅ ለብሶ በአ​መድ ላይ ቢተ​ኛም፥ ይህ ጾም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ የተ​መ​ረጠ አይ​ደ​ለም።


በአ​ም​ላ​ካ​ችን ፊት ራሳ​ች​ንን እና​ዋ​ርድ ዘንድ፥ ከእ​ር​ሱም የቀ​ና​ውን መን​ገድ ለእ​ኛና ለል​ጆ​ቻ​ችን፥ ለን​ብ​ረ​ታ​ች​ንም ሁሉ እን​ለ​ምን ዘንድ በዚያ በአ​ኅዋ ወንዝ አጠ​ገብ ጾምን አወ​ጅሁ።


“የዚ​ህም ወር ዐሥ​ረ​ኛዋ ቀን ለእ​ና​ንተ የተ​ቀ​ደ​ሰች ትሁ​ን​ላ​ችሁ፤ ሰው​ነ​ታ​ች​ሁን አስ​ጨ​ን​ቁ​አት፤ ከሥራ ሁሉ ምንም አታ​ድ​ርጉ።


የዕ​ረ​ፍት ሰን​በት ትሁ​ን​ላ​ችሁ፤ ሰው​ነ​ታ​ች​ሁ​ንም አዋ​ርዱ፤ በወሩ በዘ​ጠ​ነ​ኛው ቀን ከማታ ጀም​ራ​ችሁ እስከ ዐሥ​ረ​ኛው ቀን ማታ ድረስ፥ ሰን​በ​ታ​ች​ሁን አድ​ርጉ።”


“በዚህ በሰ​ባ​ተ​ኛው ወር ዐሥ​ረ​ኛዋ ቀን የማ​ስ​ተ​ስ​ረያ ቀን ናት፤ ቅድ​ስት ጉባኤ ትሁ​ን​ላ​ችሁ፤ ሰው​ነ​ታ​ች​ሁን አስ​ጨ​ን​ቋት፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት አቅ​ርቡ።


“ይህም የዘ​ለ​ዓ​ለም ሥር​ዐት ይሁ​ን​ላ​ችሁ።


ለጸ​ሎት እን​ድ​ት​ተጉ ከም​ት​ስ​ማ​ሙ​በት ጊዜ ብቻ በቀር፥ ባልና ሚስት አት​ለ​ያዩ፤ ዳግ​መኛ ሰይ​ጣን ድል እን​ዳ​ያ​ደ​ር​ጋ​ችሁ በአ​ን​ድ​ነት ኑሩ፤ ሰው​ነ​ታ​ችሁ ደካማ ነውና ።


ባልዋ ግን በሰ​ማ​በት ቀን ስእ​ለ​ቷን ቢከ​ለ​ክ​ላት፥ ስለ ስእ​ለቷ ወይም ራስ​ዋን ስላ​ሰ​ረ​ች​በት መሐላ ከአ​ፍዋ የወ​ጣው ነገር አይ​ጸ​ናም፤ ባልዋ ከል​ክ​ሏ​ታል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ያነ​ጻ​ታል።


ነገር ግን በየ​ዕ​ለቱ ዝም ቢላት፥ ስእ​ለ​ቷን ሁሉ፥ በእ​ር​ስ​ዋም ላይ ያለ​ውን መሐላ ሁሉ ያጸ​ና​ዋል፤ በሰ​ማ​በት ቀን ዝም ብሎ​አ​ታ​ልና አጽ​ን​ቶ​ታል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios