ዘሌዋውያን 23:32 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)32 ለእናንተ የዕረፍት ሰንበት ነው፤ ራሳችሁንም አዋርዱ፤ በወሩ በዘጠነኛው ቀን ከማታ ጀምሮ፥ ከማታ እስከ ማታ ድረስ ሰንበታችሁን አድርጉ።” Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም32 ይህ ለእናንተ የዕረፍት ሰንበት ስለ ሆነ፣ ራሳችሁን ዝቅ ዝቅ አድርጉ በወሩም ከዘጠነኛው ቀን ምሽት ጀምራችሁ እስከሚቀጥለው ቀን ምሽት ድረስ ሰንበታችሁን አክብሩ።” Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም32 ወሩ ከገባ ከዘጠነኛው ቀን የፀሐይ መጥለቂያ ሰዓት ጀምሮ እስከ ዐሥረኛው ቀን የፀሐይ መጥለቂያ ጊዜ ድረስ ለንስሓ ራሳችሁን አዋርዱ፤ ይህን ዕለት ልዩ የዕረፍት ቀን አድርጋችሁ ጠብቁት።” Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)32 የዕረፍት ሰንበት ትሁንላችሁ፤ ሰውነታችሁንም አዋርዱ፤ በወሩ በዘጠነኛው ቀን ከማታ ጀምራችሁ እስከ ዐሥረኛው ቀን ማታ ድረስ፥ ሰንበታችሁን አድርጉ።” Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)32 የዕረፍት ሰንበት ይሁንላችሁ፥ ሰውነታችሁንም አዋርዱ፤ በወሩ በዘጠነኛው ቀን በማታ ጊዜ፥ ከማታ ጀምራችሁ እስከ ማታ ድረስ፥ ሰንበታችሁን አድርጉ። Ver Capítulo |