La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘኍል 20:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እርሱም፦ “አታልፍም” አለ። ኤዶምያስም በብዙ ሕዝብና በጽኑ እጅ ሊገጥመው ወጣ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ኤዶምም እንደ ገና፣ “በዚህ ማለፍ አትችሉም” የሚል መልስ ሰጣቸው። ከዚያም ኤዶም ብዙና ኀይለኛ የሆነ ሰራዊት አሰልፎ ሊወጋቸው ወጣ፤

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ኤዶማውያን ግን “አይሆንም! አናሳልፋችሁም!” አሉ፤ ብርቱ የጦር ሠራዊትም አሰልፈው የእስራኤልን ሕዝብ ሊወጉ ወጡ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እር​ሱም፥ “በእኔ በኩል አታ​ል​ፍም” አለ። የኤ​ዶ​ም​ያ​ስም ንጉሥ በብዙ ሠራ​ዊት በጽኑ እጅ ሊገ​ጥ​መው ወጣ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እርሱም፦ አታልፍም አለ።

Ver Capítulo



ዘኍል 20:20
10 Referencias Cruzadas  

ዔሳውም አባቱ ስለ ባረከው በያዕቆብ ቂም ያዘበት፥ ዔሳውም በልቡ አለ፦ “ለአባቴ የልቅሶ ቀን ቀርቦአል፥ ከዚያም በኋላ ወንድሜን ያዕቆብን እገድለዋለሁ።”


መልእክተኞቹም ወደ ያዕቆብ ተመልሰው እንዲህ አሉት፥ “ወደ ወንድምህ ወደ ዔሳው ሄደን ነበር፥ እርሱም ደግሞ ሊቀበልህ ይመጣል፥ ከእርሱም ጋር አራት መቶ ሰዎች” አሉ።


እኔ ስለ ሰላም ስናገር፥ እነሱ ግን ስለ ጦርነት ያወራሉ።


ጌታ እንዲህ ይላል፦ “ወንድሙን በሰይፍ አሳድዶታልና፥ ርኅራኄውንም ሁሉ አጥፍቷልና፥ ባለማቋረጥም ተቆጥቷልና፥ መዓቱንም ለዘለዓለም ጠብቆአልና ስለ ሦስት የኤዶምያስ ኃጢአት ስለ አራትም መቅሠፍቴን ከማድረግ አልመለስም።


ኤዶምያስም፦ “በምድሬ ላይ አታልፍም አለበለዚያ ግን አንተን በሰይፍ ልገጥምህ እወጣለሁ” አለው።


ኤዶምያስም እስራኤል በግዛቱ ውስጥ እንዳያልፍ ከለከለ፤ ስለዚህ እስራኤል ከእርሱ ተመለሰ።


እስራኤልም ወደ ኤዶም ንጉሥ፥ ‘በአገርህ እንዳልፍ እባክህ ፍቀድልኝ’ በማለት መልእክተኞችን ላከበት፤ የኤዶም ንጉሥ ግን አልሰማውም። ለሞዓብ ንጉሥም እንደዚሁ ላከበት፤ እርሱም አልተቀበለውም፤ ስለዚህ እስራኤል በቃዴስ ተቀመጠ።


ሴዎን ግን በግዛቱ እንዲያልፍ ለመፍቀድ እስራኤልን አላመነውም፤ ሠራዊቱንም ሰብስቦ በያሃጽ ከሰፈረ በኋላ ከእስራኤል ጋር ተዋጋ።