ዘኍል 19:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በተንጣለለው ሜዳ በሰይፍ የተገደለውን ወይም የሞተውን በድን ወይም የሰውን ዐፅም ወይም መቃብር የሚነካ ማናቸውም ሰው ሰባት ቀን ርኩስ ይሆናል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ሜዳ ላይ በሰይፍ የተገደለውን ወይም እንዲሁ የሞተውን ወይም ደግሞ ዐፅም ወይም መቃብር የሚነካ ማንኛውም ሰው እስከ ሰባት ቀን ድረስ የረከሰ ይሆናል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰው የገደለውን ወይም በሕመም የሞተውን ሰው በውጭ ወድቆ ሳለ ሬሳውን የሚነካ ሰው፥ ወይም የሰው ዐፅም፥ ወይም መቃብር የሚነካ ሰው ለሰባት ቀን የረከሰ ይሆናል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሜዳም የተገደለውን ወይም የሞተውን በድን፥ ወይም የሰውን አጥንት፥ ወይም መቃብር የሚነካ ሰባት ቀን ርኩስ ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በሜዳም በሰይፍ የተገደለውን ወይም የሞተውን በድን ወይም የሰውን አጥንት ወይም መቃብር የሚነካ ሰባት ቀን ርኩስ ይሆናል። |
ጌታም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ለካህናቱ ለአሮን ልጆች እንዲህ ብለህ ለእነርሱ ተናገር፦ ማንም ሰው ከሕዝቡ መካከል ስለ ሞተው ራሱን አያርክስ፤
ከሰፈሩም ውጭ ሰባት ቀን ስፈሩ፤ ከእናንተም ሰውን የገደለ ሁሉ የተገደለውንም የነካ ሁሉ፥ በሦስተኛውና በሰባተኛው ቀን ራሳችሁንና እናንተ የማረካችኋቸውን አንጹ።
“የእስራኤል ልጆች የለምጽ ደዌ ያለበትን ሁሉ፥ ፈሳሽ ነገርም ያለበትን ሁሉ፥ ሬሳንም በመንካት የረከሰውን ሁሉ ከሰፈሩ እንዲያወጡ እዘዛቸው፤
የሞተ ሰው ሬሳን በመንካት የረከሱ ሰዎችም ነበሩ፥ ስለዚህም በዚያ ቀን የፋሲካን በዓል ለማክበር አልቻሉም ነበር። በዚያም ቀን በሙሴና በአሮን ፊት ቀረቡ።
“እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን!ወዮላችሁ፥ በውጫቸው አምረው የሚታዩ በውስጣቸው ግን በሙታን አጥንትና በርኩሰትም ሁሉ የተሞሉ በኖራ የተለሰኑ መቃብሮችን ትመስላላችሁና።