ነህምያ 2:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔም፦ “የሰማይ አምላክ ያከናውንልናል፥ እኛም አገልጋዮቹ እንነሳለን፥ እንሠራለንም፤ እናንተ ግን በኢየሩሳሌም ድርሻ ወይም መብት ወይም መታሰቢያ የላችሁም” ብዬ መለስኩላቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እኔም፣ “የሰማይ አምላክ ያከናውንልናል፤ እኛ ባሪያዎቹ እንደ ገና ሥራውን እንጀምራለን፤ እናንተ ግን በኢየሩሳሌም ድርሻ ወይም ይገባናል የምትሉት ወይም የታሪክ መታሰቢያ የላችሁም” ስል መለስሁላቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔም “የሰማይ አምላክ ሥራችንን ለማከናወን ይረዳናል፤ እኛ የእርሱ አገልጋዮች ነን፤ ስለዚህም ሥራውን እንጀምራለን፤ እናንተ ግን በኢየሩሳሌም ምንም ዐይነት ንብረት የማግኘት መብት ሆነ የታሪክ መታሰቢያነት አይኖራችሁም” ብዬ መለስኩላቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔም መልሼ፥ “የሰማይ አምላክ ያከናውንልናል፤ እኛም ንጹሓን ባሪያዎቹ ተነሥተን እንሠራለን፤ እናንተ ግን በኢየሩሳሌም ዕድል ፋንታና መብት፥ መታሰቢያም የላችሁም” አልኋቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔም መልሼ፦ “የሰማይ አምላክ ያከናውንልናል፤ እኛም ባሪያዎቹ ተነሥተን እንሠራለን፤ እናንተ ግን በኢየሩሳሌም እድል ፈንታና መብት፥ መታሰቢያም የላችሁም አልኋቸው። |
ዘሩባቤል፥ ኢያሱና የቀሩትም የእስራኤል አባቶች አለቆች፦ “የአምላካችንን ቤት ማነፅ ለእኛና ለእናንተ አይደለም፥ እኛ ለብቻችን ሆነን ንጉሥ ቂሮስ የፋርስ ንጉሥ እንዳዘዘን ለጌታ ለእስራኤል አምላክ ቤት እንገነባለን” አሉአቸው።
አሮንም ወደ መቅደስ በገባ ጊዜ ዘወትር መታሰቢያ እንዲሆን በጌታ ፊት የእስራኤልን ልጆች ስሞች በፍርዱ ደረት ኪስ ውስጥ በልቡ ላይ ይሸከም።
ወደ አሮንም ልጆች ወደ ካህናቱ ያመጣዋል። ከመልካም ዱቄቱና ከዘይቱ አንድ እፍኝ ሙሉና ዕጣኑን ሁሉ ከወሰደ በኋላ ካህኑ ለመታሰቢያ በእሳት የሚቀርብ ቁርባን አድርጎ፥ ለጌታ መዓዛው ያማረ ሽታ እንዲሆን በመሠዊያው ላይ ያቃጥለዋል።
እንዲሁም በደስታችሁ ቀን፥ በተወሰኑላችሁም የበዓላታችሁ ጊዜያት፥ በወራቱም መባቻዎቻችሁ፥ በሚቃጠል መሥዋዕታችሁና በአንድነት መሥዋዕታችሁ ላይ መለከቶቹን ንፉ፤ እነርሱም በአምላካችሁ ፊት እንድትታወሱ ይሆኑላችኋል፤ እኔ ጌታ አምላካችሁ ነኝ።”
እርሱም ትኩር ብሎ ሲመለከተው ደንግጦ “ጌታ ሆይ! ምንድነው?” አለ። መልአኩም አለው “ጸሎትህና ምጽዋትህ በእግዚአብሔር ፊት ለመታሰቢያ እንዲሆን አረገ።