La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ነህምያ 12:44 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በዚያን ቀን በይሁዳም በአገልጋዮቹ ካህናትና ሌዋውያን ደስ ስላላቸው፥ የካህናቱንና የሌዋውያኑን እድል ፈንታ እንደ ሕጉ ከከተሞች እርሻዎች ያከማቹ ዘንድ ለእጅ ማንሣት ቁርባንና ለበኵራት ለአሥራትም በየዕቃ ቤቶቹ ላይ በዚያ ቀን ሰዎች ተሾሙ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በዚያ ቀን ስጦታው፣ በኵራቱና ዐሥራቱ የሚቀመጥበትን ዕቃ ቤት የሚጠብቁ ሰዎች ተሾሙ። እነርሱም በየከተሞች ዙሪያ ከሚገኙት የዕርሻ ቦታዎች ሕጉ በሚያዝዘው መሠረት የካህናቱንና የሌዋውያኑን ድርሻ ወደ ዕቃ ቤቱ ማምጣት ነበረባቸው፤ ይሁዳ በሚያገለግሉ ካህናትና ሌዋውያን ደስ ተሠኝተው ነበርና።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በዚያም ጊዜ ለቤተ መቅደስ መገልገያ የሚደረገውን አስተዋጽዖ እንዲሁም ከዐሥር አንዱን፥ በየዓመቱ በመጀመሪያ የሚደርሰውን እህልና ፍራፍሬ በማከማቸት የዕቃ ቤት ክፍሎችን የሚጠብቁ ኀላፊዎች ተሾሙ፤ እነዚህም ሰዎች በልዩ ልዩ ከተሞች አቅራቢያ ከሚገኙ የእርሻ ቦታዎች ሕጉ በሚያዝዘው መሠረት ለካህናቱና ለሌዋውያኑ የተመደበውን አስተዋጽዖ የመሰብሰብ ኀላፊነት ነበራቸው፤ የይሁዳም ሕዝብ በሙሉ በካህናቱና በሌዋውያኑ እጅግ ደስ ብሎአቸው ነበር።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የይ​ሁ​ዳም ሕዝብ በአ​ገ​ል​ጋ​ዮቹ ካህ​ና​ትና ሌዋ​ው​ያን ደስ ስላ​ላ​ቸው፥ የካ​ህ​ና​ቱ​ንና የሌ​ዋ​ው​ያ​ኑን ዕድል ፈንታ እንደ ሕጉ ከከ​ተ​ሞች እር​ሻ​ዎች ያከ​ማቹ ዘንድ ለቀ​ዳ​ም​ያት፥ ለዐ​ሥ​ራ​ትም በየ​ዕቃ ቤቶቹ ላይ በዚያ ቀን ሰዎ​ችን ሾሙ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ይሁዳም በአገልጋዮቹ ካህናትና ሌዋውያን ደስ ስላላቸው፥ የካህናቱንና የሌዋውያኑን እድል ፈንታ እንደ ሕጉ ከከተሞች እርሻዎች ያከማቹ ዘንድ ለእጅ ማንሣት ቁርባንና ለበኩራት ለአሥራትም በየዕቃ ቤቶቹ ላይ በዚያ ቀን ሰዎች ተሾሙ።

Ver Capítulo



ነህምያ 12:44
17 Referencias Cruzadas  

“ሥራቸውም የጌታን ቤት በየአደባባዩና በየጓዳው ውስጥ በሚሰጡተት አገልግሎት አሮንን ልጆች መርዳት፥ ቅዱሱንም ዕቃ ሁሉ ማንጻት፥ የእግዚአብሔርንም ቤት አገልግሎት መሥራት ነበረ።


ከሌዋውያን አኪያ በእግዚአብሔር ቤት በሚሆኑ ቤተ መዛግብትና በንዋየ ቅዱሳቱ ቤተ መዛግብት ላይ ተሾሞ ነበር።


ከሌዋውያንም የነበሩ አራቱ የጠባቂዎች አለቆች በሥራቸው ታማኞች ነበሩ፤ በጌታም ቤት ባሉ ጓዳዎችና ቤተ መዛግብት ላይ ተሹመው ነበር።


በሕጉም እንደ ተጻፈ የልጆቻችንና የእንስሶቻችንን በኵራት፥ የበሬዎቻችንንና የበጎቻችንን በኵራት፥ በአምላካችን ቤት ወደ ሚያገለግሉት ካህናት ወደ አምላካችን ቤት እናመጣ ዘንድ፥


የሚሰማኝ ሰው ምስጉን ነው ዕለት ዕለት በቤቴ መግቢያ የሚተጋ፥ የደጄንም መድረክ የሚጠብቅ።


ጌታን በመተማመን የሚጠባበቁ ግን ኃይላቸውን ያድሳሉ፤ እንደ ንስር በክንፍ ይወጣሉ፤ ይሮጣሉ፤ አይታክቱም፤ ይሄዳሉ፤ አይደክሙም።


አሮንንና ልጆቹን ሹማቸው፥ ክህነታቸውንም ይጠብቁ፤ ማናቸውም ሌላ ሰው ግን ቢቀርብ ይገደል።”


አገልግሎት ከሆነ ማገልገል፤ ማስተማር ከሆነ ማስተማር፤


ከቤተሰቡ ንብረት ሽያጭ ላይ ገንዘብ ቢቀበል እንኳን ባልንጀሮቹ ከሚያገኙት ጥቅም እኩል ይካፈላል።