ነህምያ 11:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በእግዚአብሔር ቤት ሥራ ላይ ከነበሩ መዘምራን ከአሳፍ ልጆች ወገን የሚካ ልጅ፥ የማታንያ ልጅ፥ የሓሻብያ ልጅ፥ የባኒ ልጅ ዑዚ በኢየሩሳሌም የሌዋውያን አለቃ ነበረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በኢየሩሳሌም የሌዋውያኑ ዋና አለቃ የሚካ ልጅ፣ የመታንያ ልጅ፣ የሐሸብያ ልጅ፣ የባኒ ልጅ ኦዚ ነበረ፤ ኦዚ በእግዚአብሔር ቤት አገልግሎት ለሚዘመረው መዝሙር ኀላፊ ከነበሩት ከአሳፍ ዘሮች አንዱ ነበረ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በኢየሩሳሌም የሌዋውያን አለቃ ዑዚ የባሂ ልጅ፥ የሖሻብያ ልጅ፥ የማታንያ ልጅ፥ የሚካ ልጅ ነበር። ዑዚ የቤተ መቅደስ መዘምራን ኀላፊ የነበረው የአሳፍ ዘር ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በእግዚአብሔርም ቤት ሥራ ላይ ከነበሩ መዘምራን ከአሳፍ ልጆች ወገን የሚካ ልጅ፥ የመታንያ ልጅ፥ የሐሳብያ ልጅ፥ የባኒ ልጅ ኦዚ በኢየሩሳሌም የሌዋውያን አለቃ ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በእግዚአብሔርም ቤት ሥራ ላይ ከነበሩ መዘምራን ከአሳፍ ልጆች ወገን የሚካ ልጅ የመታንያ ልጅ የሐሸብያ ልጅ የባኒ ልጅ አዚ በኢየሩሳሌም የሌዋውያን አለቃ ነበረ። |
በዕቃ ቤቶችም ላይ ካህኑን ሰሌምያን፥ ጸሐፊውንም ሳዶቅን፥ ከሌዋውያኑም ፈዳያን ሾምሁ፥ ከእነርሱም ጋር የማታንያ ልጅ የዘኩር ልጅ ሐናን ነበረ፥ እነርሱም የታመኑ ሆነው ተገኙ፥ ሥራቸውም ለወንድሞቻቸው ማከፋፈል ነበረ።
ደግሞ ኢያሱ፥ ባኒ፥ ሼሬብያ፥ ያሚን፥ ዓቁብ፥ ሻብታይ፥ ሆዲያ፥ ማዓሤያ፥ ቅሊጣ፥ አዛርያ፥ ዮዛባድ፥ ሐናን፥ ፐላያና ሌዋውያኑ ሕጉን ለሕዝቡ ያስረዱ ነበር፤ ሕዝቡም በቆሙበት ነበሩ።
በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቁአት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ኤጲስ ቆጶሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ።