ናሆም 3:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለደም ከተማ ወዮላት! በሁለንተናዋ ማታለልና ዘረፋ ሞልቶባታል፤ ንጥቂያ ከእርሷ አይርቅም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለደም ከተማ ወዮላት! ሐሰት፣ ዘረፋም ሞልቶባታል፤ ብዝበዛዋ ተግዞ አያልቅም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለነፍሰ ገዳዮች ከተማ፥ ፈጽማ አታላይ ለሆነች፥ በዝርፊያ ለታወቀችና በብዙ ምርኮ ለተሞላች ለነነዌ ከተማ ወዮላት! የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለደም ከተማ ወዮላት! በሁለንተናዋ ሐሰትና ቅሚያ ሞልቶባታል፣ ንጥቂያ ከእርስዋ አያልቅም። |
ያዕቆብን ለማረኩ እስራኤልንም ለበዘበዙ ሰዎች የሰጠ ማን ነው? እኛ የበደልነው፥ እነርሱም በመንገዱ ለመሄድ ያልወደዱት፥ ለሕጉም ያልታዘዙለት ጌታ እርሱ አይደለምን?