Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ናሆም 3:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 ለነፍሰ ገዳዮች ከተማ፥ ፈጽማ አታላይ ለሆነች፥ በዝርፊያ ለታወቀችና በብዙ ምርኮ ለተሞላች ለነነዌ ከተማ ወዮላት!

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 ለደም ከተማ ወዮላት! ሐሰት፣ ዘረፋም ሞልቶባታል፤ ብዝበዛዋ ተግዞ አያልቅም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ለደም ከተማ ወዮላት! በሁለንተናዋ ማታለልና ዘረፋ ሞልቶባታል፤ ንጥቂያ ከእርሷ አይርቅም።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 ለደም ከተማ ወዮላት! በሁለንተናዋ ሐሰትና ቅሚያ ሞልቶባታል፣ ንጥቂያ ከእርስዋ አያልቅም።

Ver Capítulo Copiar




ናሆም 3:1
11 Referencias Cruzadas  

በብዝበዛ አትመኩ፤ በቀማችሁትም ነገር ለመክበር ተስፋ አታድርጉ፤ ሀብታችሁ ቢበዛ እንኳ በእርሱ አትተማመኑ።


በምሽት ጊዜ እነሆ፥ ሽብር ይሆናል፤ በማለዳ ግን ይጠፋሉ፤ የሚዘርፉንና የሚበዘብዙን ሰዎችም ዕድል ፈንታ ይኸው ነው።


የወይን ጠጅ እየጠጡ በመዝፈን መደሰት አይኖርም፤ የሚያሰክር መጠጥም ለጠጪው መራራ ይሆናል።


የያዕቆብን ልጆች እስራኤላውያንን ለዘራፊና ለቀማኛ አሳልፎ የሰጠ ማነው? ይህን ያደረገው እግዚአብሔር ራሱ አይደለምን? ይህም የሆነው እኛ ስለ በደልነው፥ በሚፈቅደው መንገድ ስላልሄድንና ለሕጉም ታዛዦች ስላልሆንን ነው።


በመሐላ የገቡትን ቃል ኪዳን አፍርሰው ይዋሻሉ፤ ይገድላሉ፤ ይሰርቃሉ፤ ያመነዝራሉም፤ ግፍና ግድያ እየበዛ ሄዶአል።


አንበሳ ለግልገሎቹ የሚበቃቸውን ያኽል ዐድኖ አመጣ፤ ለእንስቲቱ አንበሳም የምትመገበውን ገድሎ አመጣላት፤ ዋሻውን በታደኑ እንስሶች ጒድጓዱንም በተቦጫጨቀ ሥጋ ሞላ።


ነነዌ ሆይ! በአንቺ ላይ ተነሥቼአለሁ ይላል የሠራዊት አምላክ፤ ሠረገሎችሽንም አቃጥላለሁ፤ ደቦሎችሽንም ሰይፍ ይበላቸዋል፤ በምድር ላይ በአንቺ ተጠቂ የሚሆን እንዳይኖር አደርጋለሁ፤ የመልእክተኞችሽም ድምፅ ከእንግዲህ ወዲያ አይሰማም።


ሰውን በመግደል ከተማን ለምትቈረቊሩና፥ በበደል ዋና ከተማን ለምትሠሩ ወዮላችሁ!


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos