ናሆም 2:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጦረኞቹ ጋሻ ቀልቶአል፥ ኃያላን ሰዎችም ቀይ ልብስ ለብሰዋል። እርሱ በሚያዘጋጅበት ቀን ሰረገሎች እንደ እሳት ይንቦገቦጋሉ፥ ጦሮቹም ይወዘወዛሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሠረገሎች በአደባባይ ወዲያ ወዲህ ይከንፋሉ፤ በመንገዶችም ላይ ይርመሰመሳሉ፤ የሚንበለበል ፋና ይመስላሉ፤ እንደ መብረቅም ይወረወራሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሠረገሎቹ በከፍተኛ ፍጥነት በመንገዶች ይሽቀዳደማሉ፤ በአደባባዩም ላይ ወዲያና ወዲህ ይጣደፋሉ፤ የሚንቦገቦግ ችቦም ይመስላሉ፤ እንደ መብረቅም ይወረወራሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰረገሎች በመንገድ ላይ ይነጕዳሉ፥ አደባባይም ይጋጫሉ፣ መልካቸው እንደ ፋና ነው፥ እንደ መብረቅም ይከንፋሉ። |
አንተም እንዲህ አለክ፦ በሠረገላዬ ብዛት ወደ ተራሮች ከፍታ፥ ወደ ሲባኖስ ጥግ ወጥቻለሁ፤ ረጃጅሞቹን ዝግባዎች፥ የተመረጡትን ጥንዶች እቈርጣለሁ፥ ወደ ከፍታውም ዳርቻ ወደ ቀርሜሎስ ዱር እገባለሁ፤
መሣሪያ፥ ሠረገላና መንኰራኵር ይዘው፥ ብዙ ሕዝብ ሆነው በአንቺ ላይ ይመጣሉ፤ ጋሻና አላባሽ ጋሻ ራስ ቁርም ይዘው በዙሪያሽ ይዘጋጁብሻል፥ ፍርድንም እሰጣቸዋለሁ፥ እንደ ፍርዳቸውም ይፈርዱብሻል።
ከፈረሶቹ ብዛት የተነሣ አቧራቸው ይሸፍንሻል፤ ሰዎች ወደ ፈረስች ከተማ እንደሚገቡ እርሱ በበሮችሽ በሚገባበት ጊዜ፥ ከፈረሰኞች፥ ከመንኩራኩሮች እና ከሰረገሎች ድምፅ የተነሣ ቅጥሮችሽ ይናወጣሉ።
ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ እነሆ ከሰሜን የነገሥታት ንጉሥ የሆነውን የባቢሎንን ንጉሥ ናቡከደነዖርን ከፈረሶች፥ ከሰረገሎች፥ ከፈረሰኞች፥ ከጉባኤና ከብዙ ሕዝብ ጋር በጢሮስ ላይ አመጣለሁ።