ሕዝቅኤል 23:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)24 መሣሪያ፥ ሠረገላና መንኰራኵር ይዘው፥ ብዙ ሕዝብ ሆነው በአንቺ ላይ ይመጣሉ፤ ጋሻና አላባሽ ጋሻ ራስ ቁርም ይዘው በዙሪያሽ ይዘጋጁብሻል፥ ፍርድንም እሰጣቸዋለሁ፥ እንደ ፍርዳቸውም ይፈርዱብሻል። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም24 እነርሱም የጦር መሣሪያ፣ ሠረገላና ጋሪ በመያዝ ብዙ ሕዝብ ሆነው ይመጡብሻል፤ ትላልቅና መለስተኛ ጋሻ በማንገብና የራስ ቍር በመድፋት በየአቅጣጫው ይሰለፉብሻል፤ እኔም ለፍርድ በእጃቸው አሳልፌ እሰጥሻለሁ፤ በሕጋቸውም መሠረት ይቀጡሻል። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም24 እነርሱም በብዙ ሠረገላና ስንቅ በተጫኑ ጋሪዎች የተጠናከረ ታላቅ ሠራዊት መርተው በማምጣት በሁሉም አቅጣጫ አደጋ ይጥሉብሻል፤ በጋሻና በራስ ቊር እየተከላከሉ ይከቡሻል፤ እኔም ለእነርሱ ፍርድ አሳልፌ እሰጥሻለሁ፤ እነርሱም በራሳቸው ሕግ መሠረት ይቀጡሻል። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)24 ስማቸውን ያስጠሩ ሰዎች ሁሉ በመንኰራኵርና በሠረገላ፥ በአሕዛብም ጉባኤ ይመጡብሻል፤ ጋሻና አላባሽ ጋሻ፥ ራስ ቍርም ይዘው በዙሪያሽ ጥበቃ ያደርጋሉ፤ ፍርድንም እሰጣቸዋለሁ፤ እንደ ፍርዳቸውም ይፈርዱብሻል። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)24 በመሣሪያና በሰረገላ በመንኰራኵርም በአሕዛብም ጉባኤ ይመጡብሻል፥ ጋሻና አላባሽ ጋሻ ራስ ቍርም ይዘው በዙሪያሽ ይዘጋጁብሻል፥ ፍርድንም እሰጣቸዋለሁ፥ እንደ ፍርዳቸውም ይፈርዱብሻል። Ver Capítulo |