ሚክያስ 7:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሕዛብ ያያሉ፥ በኀይላቸው ሁሉ ያፍራሉ፤ እጃቸውን በአፋቸው ላይ ያኖራሉ፥ ጆሮዎቻቸውም ይደነቁራሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አሕዛብ ያያሉ፣ ያፍራሉም፤ ኀይላቸውን ሁሉ ያጣሉ፤ አፋቸውን በእጃቸው ይይዛሉ፤ ጆሯቸውም ትደነቍራለች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኀይል ያላቸው ቢሆኑም ይህን አይተው ያፍራሉ፤ እጆቻቸውን በአፋቸው ላይ ያኖራሉ፤ ጆሮዎቻቸውንም ይደፍናሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሕዛብ አይተው በጕልበታቸው ሁሉ ያፍራሉ፥ እጃቸውን በአፋቸው ላይ ያኖራሉ፥ ጆሮአቸውም ትደነቍራለች፥ እንደ እባብም መሬት ይልሳሉ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሕዛብ አይተው በጕልበታቸው ሁሉ ያፍራሉ፥ እጃቸውን በአፋቸው ላይ ያኖራሉ፥ ጆሮአቸውም ትደነቍራለች፥ እንደ እባብም መሬት ይልሳሉ፥ |
የመንግሥታትንም ዙፋን እገለብጣለሁ፥ የአሕዛብ መንግሥታትን ኃይል አጠፋለሁ፤ ሰረገሎችንና ነጂዎቻቸውን እገለብጣለሁ፤ ፈረሶችንና ፈረሰኞቻቸው እያንዳንዱ በወንድሙ ሰይፍ ይወድቃሉ።
ነገር ግን አፍ ሁሉ እንዲዘጋና ዓለምም ሁሉ ከእግዚአብሔር ፍርድ ሥር እንዲሆን፤ ሕግ የሚናገረው ሁሉ ከሕግ በታች ላሉት እንደሚናገር እናውቃለን፤
አሕዛብም ተቈጡ፤ ቁጣህም መጣ፤ በሙታንም የምትፈርድበት ዘመን መጣ፤ ለባርያዎችህም ለነቢያትና ለቅዱሳን፥ ስምህንም ለሚፈሩት ለታናናሾችና ለታላላቆችም ዋጋቸውን የምትሰጥበት ምድርንም የሚያጠፉትን የምታጠፋበት ዘመን መጣ።”