ዘሌዋውያን 9:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለአንድነትም መሥዋዕት በሬንና አውራን በግ፥ በዘይትም የተለወሰ የእህልን ቁርባን በጌታ ፊት ለመሠዋት ውሰዱ፥ ዛሬ ጌታ ተገልጦላችኋልና።’ ” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለኅብረት መሥዋዕት አንድ በሬና አንድ አውራ በግ በዘይት ከተለወሰ የእህል ቍርባን ጋራ በእግዚአብሔር ፊት ለመሠዋት አቅርቡ፤ እግዚአብሔር ዛሬ ይገለጥላችኋልና።’ ” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲሁም አንድ ወይፈንና አንድ የበግ ጠቦት ለአንድነት መሥዋዕት ያምጡ፤ እነዚህንም በዘይት ከታሸ የእህል መባ ጋር ለእግዚአብሔር መሥዋዕት አድርገው ያቅርቡ፤ ዛሬ እግዚአብሔር ስለሚገለጥላቸው ይህን ሁሉ ያድርጉ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለደኅንነትም መሥዋዕት በሬንና አውራ በግን፥ በዘይትም የተለወሰ የእህልን ቍርባን በእግዚአብሔር ፊት ይሠዉ ዘንድ ውሰዱ፤ ዛሬ እግዚአብሔር ይገለጥላችኋልና ብለህ ንገራቸው።” |
ቀኖቹንም በፈጸሙ ጊዜ በስምንተኛው ቀንና ከዚያም በኋላ፥ ካህናቱ የሚቃጠል መሥዋዕታችሁንና የሰላም መሥዋዕታችሁን በመሠዊያው ላይ ያደርጋሉ፤ እኔም እቀበላችኋለሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
ለእስራኤልም ልጆች እንዲህ ብለህ ትናገራለህ፦ ‘ለኃጢአት መሥዋዕት አውራ ፍየልን፥ ለሚቃጠልም መሥዋዕት ነውር የሌለባቸውን አንድ ዓመት የሆናቸውን እምቦሳና ጠቦትን፥