ዘሌዋውያን 3:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ካህኑም ለጌታ በእሳት ላይ የሚቀርብ ማዕድ አድርጎ በመሠዊያው ላይ ያቃጥለዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ካህኑም ይህን ሁሉ ለእግዚአብሔር በእሳት የሚቀርብ የመብል ቍርባን አድርጎ በመሠዊያው ላይ ያቃጥል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ካህኑም ይህን ሁሉ ለእግዚአብሔር የምግብ መባ አድርጎ በማቅረብ በመሠዊያው ላይ ያቃጥለዋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ካህኑም በመሠዊያው ላይ ያቀርበዋል፤ በጎ መዓዛ ያለው ለእግዚአብሔር የሚቃጠል መሥዋዕት ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ካህኑም በመሠዊያው ላይ ያቃጥለዋል፤ በእሳት ላይ ለእግዚአብሔር የተደረገ የቍርባን መብል ነው። |
ምግቤን፥ ስብንና ደምን፥ በምታቀርቡበት ጊዜ ቤቴን እንዲያረክሱ በመቅደሴ ውስጥ እንዲሆኑ ያልተገረዘ ልብ፥ ያልተገረዘ ሥጋ ያላቸውን ባዕዳንን አግብታችኋል፥ በርኩሰታችሁም ሁሉ ቃል ኪዳኔን አፍርሰዋል።
ለአምላካቸው የተቀደሱ ይሆናሉ፥ የአምላካቸውንም ስም አያረክሱም፤ እነርሱም የአምላካቸው እንጀራ የሆነውን፥ ለጌታ በእሳት የሚቀርበውን ቁርባን ያቀርባሉና የተቀደሱ ይሆናሉ።
ከእንግዳም ሰው እጅ የተገኙ እንደነዚህ ያሉ እንስሶችን ሁሉ ለአምላካችሁ እንጀራ እንዲሆኑ አታቅርቡ፤ ርኩሰትም ነውርም አለባቸውና አይሠምሩላችሁም።”
የአሮንም ልጆች ከሚቃጠል መሥዋዕት ጋር በመሠዊያው ላይ በእሳቱ ላይ ባለው በእንጨቱ ላይ ያቃጥሉታል፤ ለጌታ መዓዛው ያማረ ሽታ የሆነ በእሳት የሚቀርብ ቁርባን ነው።
“በመሠዊያዬ ላይ የረከሰ ምግብ ታቀርባላችሁ።” እናንተም፦ “ያረከስንህ እንዴት ነው?” ትላላችሁ። “የጌታ ገበታ የተናቀ ነው” በማለታችሁ ነው።
የእስራኤልን ልጆች እንዲህ ብለህ እዘዛቸው፦ “‘ማዕዴን፥ ለእኔ መዓዛው ያማረ ሽታ እንዲሆን በእሳት የሚቀርበውን ቁርባኔን፥ መባዬን በተገቢው ጊዜ እንድታቀርቡልኝ በጥንቃቄ ልብ በሉ።’
ለጌታ መዓዛው ያማረ ሽታ እንዲሆን በእሳት የሚቀርበውን የቁርባኑን ማዕድ ሰባት ቀን በየዕለቱ እንዲሁ ታቀርባላችሁ፤ ዘወትር ከሚቃጠለው መሥዋዕትና ከመጠጡ ቁርባን ጎን ለጎን የሚቀርብ ይሆናል።
እነሆ በደጅ ቆሜ አንኳኳለሁ፤ ማንም ድምፄን ቢሰማ ደጁንም ቢከፍትልኝ፥ ወደ እርሱ እገባለሁ፤ ከእርሱም ጋር እራት እበላለሁ፤ እርሱም ከእኔ ጋር ይበላል።