ዘሌዋውያን 3:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)5 የአሮንም ልጆች ከሚቃጠል መሥዋዕት ጋር በመሠዊያው ላይ በእሳቱ ላይ ባለው በእንጨቱ ላይ ያቃጥሉታል፤ ለጌታ መዓዛው ያማረ ሽታ የሆነ በእሳት የሚቀርብ ቁርባን ነው። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም5 የአሮንም ልጆች በመሠዊያው በሚነድደው ዕንጨት ላይ ባለው በሚቃጠለው መሥዋዕት ላይ አድርገው ያቃጥሉት፤ ይህም በእሳት የሚቀርብ፣ ሽታውም እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ መሥዋዕት ይሆናል። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም5 ይህ የሚቃጠል መሥዋዕት በመሆኑ የአሮን ልጆች በሚቃጠለው መሥዋዕት መሠዊያ ላይ ያቃጥሉት፤ ይህ ዐይነቱ መሥዋዕት መዓዛው እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ነው። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)5 የአሮንም ልጆች ከሚቃጠል መሥዋዕት ጋር በመሠዊያው ላይ በእሳቱ ላይ ባለው በዕንጨቱ ላይ ያቀርቡታል፤ የእሳት ቍርባን ለእግዚአብሔር በጎ መዓዛ ነው። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)5 የአሮንም ልጆች ከሚቃጠል መሥዋዕት ጋር በመሠዊያው ላይ በእሳቱ ላይ ባለው በእንጨቱ ላይ ያቃጥሉታል፤ የእሳት ቍርባን ለእግዚአብሔር ጣፋጭ ሽታ ነው። Ver Capítulo |