በኤርምያስ አንደበት የተናገረው የጌታ ቃል እንዲፈጸም፥ ምድሪቱ ሰንበትን በማድረግዋ እስክታርፍ ድረስ፤ በተፈታችበትም ዘመን ሁሉ፥ ሰባ ዓመት እስኪፈጸም ድረስ፥ ሰንበትን አደረገች።
ዘሌዋውያን 25:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ለእነርሱ ተናገር፦ እኔ ወደምሰጣችሁ ምድር በገባችሁ ጊዜ ምድሪቱ ለጌታ ሰንበት ታድርግ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ለእስራኤላውያን እንዲህ ብለህ ተናገር፤ ‘ወደምሰጣችሁ ምድር በምትገቡበት ጊዜ ምድሪቱ ራሷ የእግዚአብሔርን ሰንበት ታክብር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ለእስራኤላውያን እንዲህ በላቸው፦ እኔ እግዚአብሔር ወደምሰጣችሁ ምድር በምትገቡበት ጊዜ በሰባተኛው ዓመት ምንም ሳታርሱ ምድሪቱን በማሳረፍ እግዚአብሔርን ታከብራላችሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ እኔ ወደምሰጣችሁ ምድር በገባችሁ ጊዜ እኔ የምሰጣችሁ ምድር ታርፋለች፤ ለእግዚአብሔርም ሰንበት ታደርጋለች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ እኔ ወደምሰጣችሁ ምድር በገባችሁ ጊዜ ምድሪቱ ለእግዚአብሔር ሰንበት ታድርግ። |
በኤርምያስ አንደበት የተናገረው የጌታ ቃል እንዲፈጸም፥ ምድሪቱ ሰንበትን በማድረግዋ እስክታርፍ ድረስ፤ በተፈታችበትም ዘመን ሁሉ፥ ሰባ ዓመት እስኪፈጸም ድረስ፥ ሰንበትን አደረገች።
እየጠራረገ ወደ ይሁዳ ይወርዳል፤ እያጥለቀለቀ ያልፋል፤ እስከ ዐንገትም ይደርሳል፤ አማኑኤል ሆይ፤ የተዘረጉ ክንፎቹ ምድርህን ከዳር እስከ ዳር ይሸፍናሉ።”
ምድሪቱን በምድርም ፊት ላይ ያሉትን ሰዎችንና እንስሶችን በታላቅ ኃይሌና በተዘረጋችው ክንዴ የፈጠርሁ እኔ ነኝ፤ ለዓይኔም መልካም ለሆነው እሰጣታለሁ።
“ከኢያሪኮ ማዶ ባለው የሞዓብ ምድር፥ ከዓባሪም ተራራዎች አንዱ ወደ ሆነው ወደ ነቦ ተራራ ውጣ፥ ለእስራኤላውያን ርስት አድርጌ የምሰጣትን የከነዓንን ምድር አሻግረህ ተመልከት።
ጌታም፦ “ለዘርህ እሰጣታለሁ ብዬ ለአብርሃምና ለይስሐቅ ለያዕቆብም የማልሁላቸው ምድር ይህች ናት፥ በዓይንህ እንድታያት አደረግሁህ፥ ነገር ግን ወደዚያች አትሻገርም” አለው።