በቅድስተ ቅዱሳኑ ፊት ለፊት አምስቱ በስተ ደቡብ፥ አምስቱ ደግሞ በስተ ሰሜን የሚቀመጡት ዐሥሩ የወርቅ መቅረዞች፥ አበባዎች፥ የመብራት ቀንዲሎች፥ የእሳት መቆስቆሻዎች፥
ዘሌዋውያን 24:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በጌታ ፊት በንጹሕ የወርቅ መቅረዝ ላይ መብራቶቹን ሁልጊዜ ያዘጋጃል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በእግዚአብሔር ፊት በንጹሕ የወርቅ መቅረዝ ላይ ያሉት መብራቶች ያለ ማቋረጥ መሰናዳት አለባቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አሮን መብራቶቹን በንጹሕ የወርቅ መቅረዝ ላይ በእግዚአብሔር ፊት ባለሟቋረጥ የሚበሩ መሆናቸውንም ይቈጣጠራል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በእግዚአብሔር ፊት በጥሩ መቅረዝ ላይ መብራቶቹን ሁል ጊዜ እስኪነጋ አብሩአቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በእግዚአብሔር ፊት በጥሩ መቅረዝ ላይ መብራቶቹን ሁልጊዜ ያሰናዳቸው። |
በቅድስተ ቅዱሳኑ ፊት ለፊት አምስቱ በስተ ደቡብ፥ አምስቱ ደግሞ በስተ ሰሜን የሚቀመጡት ዐሥሩ የወርቅ መቅረዞች፥ አበባዎች፥ የመብራት ቀንዲሎች፥ የእሳት መቆስቆሻዎች፥
ለወርቁም መቅረዞችና ለቀንዲሎቹም ወርቁን በየመቅረዙና በየቀንዲሉ በሚዛን ሰጠው፤ ለብሩም መቅረዞች እንደ መቅረዙ ሁሉ ሥራ ብሩን በየመቅረዙና በየቀንዲሉ በሚዛን ሰጠው፤
ደግሞም ዋና የመግቢያ ደጆችን ዘጉ፥ መብራቶቹንም አጥፍተዋል፥ በመቅደሱም ውስጥ ለእስራኤል አምላክ አላጠኑም፥ የሚቃጠለውንም መሥዋዕት አላቀረቡም።
የዘበኞቹም አለቃ ወጭቶቹንና ማንደጃዎቹን፥ ጐድጓዳ ሳሕኖቹንና የሸክላ ድስቶቹን፥ መቅረዞችንና ሙዳዮችን መንቀሎችንም፥ የወርቁን ዕቃ በወርቅ፥ የብሩንም ዕቃ በብር አድርጎ፥ ወሰደ።
አሮን ከማታ እስከ ማለዳ ድረስ በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ከምስክሩ መጋረጃ ውጭ በጌታ ፊት ሁልጊዜ ያዘጋጀው፤ ለዘለዓለም ለልጅ ልጃችሁ ሥርዓት ይሁን።
ታቦቱንም፥ ገበታውንም፥ መቅረዙንም፥ መሠዊያዎቹንም፥ ካህናቱም የሚገለገሉባቸውን የመቅደሱን ዕቃዎች፥ መጋረጃውንም፥ መገልገያውንም ሁሉ ይጠብቃሉ።
ሰማያዊውንም መጐናጸፊያ ይውሰዱ፥ የመብራቱንም መቅረዝ፥ ቀንዲሎቹንም፥ መቆንጠጫዎቹንም፥ መተርኮሻዎቹንም፥ ዘይቱንም የሚያቀርቡባቸውን ዕቃዎች ሁሉ ይሸፍኑ፤
በቀኝ እጄ ያየሃቸው የሰባቱ ከዋክብትና የሰባቱ የወርቅ መቅረዞች ምሥጢር ይህ ነው፤ ሰባቱ ከዋክብት የሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት መላእክት ናቸው፤ ሰባቱም መቅረዞች ሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት ናቸው።”
እንግዲህ ከየት እንደ ወደቅህ አስብ፤ ንስሓም ግባ፥ የቀደመውንም ሥራህን አድርግ፤ አለዚያ እመጣብሃለሁ ንስሓም ባትገባ መቅረዝህን ከስፍራው እወስዳለሁ።