La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘሌዋውያን 22:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በእርሱም እንዳይረክስ፥ የሞተውን አውሬም የገደለውን አይብላ፤ እኔ ጌታ ነኝ።’

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እንዳይረክስ ማንኛውንም ሞቶ የተገኘውን ወይም አውሬ የዘነጠለውን አይብላ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ሞቶ የተገኘውን ወይም አውሬ የገደለውን የእንስሳ ሥጋ አይብላ፤ እርሱን ቢበላ ያረክሰዋል፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በእ​ር​ሱም እን​ዳ​ይ​ረ​ክስ፥ የሞ​ተ​ውን፥ አው​ሬም የሰ​በ​ረ​ውን አይ​ብላ፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝና።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በእርሱም እንዳይረክስ፥ የሞተውን አውሬም የሰበረውን አይብላ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።

Ver Capítulo



ዘሌዋውያን 22:8
8 Referencias Cruzadas  

ቅዱስ ወገን ትሆኑልኛላችሁ፤ ስለዚህ በሜዳ አውሬ የገደለውን ሥጋ አትብሉ፤ ለውሻ ጣሉት።


እኔም እንዲህ አልሁ፦ ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፥ ወይኔ! እነሆ፥ ሰውነቴ አልረከሰችም፥ ከልጅነቴ ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ፥ የሞተ ወይም እንስሳ የገደለውን ከቶ አልበላሁም፥ ርኩስም ሥጋ በአፌ ውስጥ አልገባም።


ካህናቱ የሞተ ወይም ሌላ አውሬ የገደለውን ወፍ ወይም እንስሳ አይብሉ።


የሞተውን ወይም አውሬ የገደለውን የሚበላ ሰው ሁሉ፥ የአገሩ ተወላጅ ወይም እንግዳ ቢሆን፥ ልብሱን ያጥባል፥ በውኃም ይታጠባል፥ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሆናል፤ ከዚያም በኋላ ንጹሕ ይሆናል።


ሞቶ የተገኘን የእንስሳ ስብ፥ እንዲሁም አውሬ የገደለውን የእንስሳ ስብ ለማናቸውም ለሌላ ተግባር አድርጉት እንጂ ከእርሱ ፈጽሞ ምንም አትብሉ፤


“አንተ ግን ለጌታ ለእግዚአብሔር ቅዱስ ሕዝብ ነህና የሞተውን ሁሉ አትብላ፤ ከከተሞችህ በአንዲቱ ለሚኖር መጻተኛ እንዲበላ ልትሰጠው ትችላለህ፤ ወይም ለውጭ አገር ሰው ልትሸጠው ትችላለህ። የፍየልን ግልገል በእናቱ ወተት አትቀቅል።