ዘሌዋውያን 22:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ማናቸውም ምእመን ከተቀደሰው አይብላ የካህኑም እንግዳ የሆነ እና ተቀጥሮ የሚያገለግል ከተቀደሰው አይብላ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘ከካህን ቤተ ሰብ በቀር የካህኑ እንግዳም ሆነ ቅጥር ሠራተኛ የተቀደሰውን መሥዋዕት አይብላ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ከተቀደሰው ስጦታ መብላት የሚችለው የካህን ቤተሰብ የሆነ ሰው ብቻ ነው፤ ሌላ ሰው ግን ከእርሱ አይብላ፤ ከካህኑ ጋር በእንግድነት ወይም ተቀጥሮ የሚኖር አይብላ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ከባዕድ ወገን የሆነ ሰው ከተቀደሰው አይብላ፤ የካህኑም እንግዳ፥ ደመወዘኛውም ከተቀደሰው አይብላ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ልዩ ሰው ከተቀደሰው አይብላ የካህኑም እንግዳ ደመወዘኛውም ከተቀደሰው አይብላ። |
የካህን ልጅ ግን ባልዋ ቢሞት፥ ወይም ብትፋታ፥ ልጅም ባይኖራት፥ በብላቴንነትዋ እንደ ነበረች ወደ አባትዋ ቤት ብትመለስ፥ ከአባትዋ እንጀራ ትብላ፤ ማናቸውም ምእመን ግን ከእርሱ አይብላ።
ስለዚህ ካህኑ የተቀደሰውን እንጀራ ለዳዊት ሰጠው፤ ከጌታ ፊት ተነሥቶ በትኩስ እንጀራ ከተተካው ከኅብስት በስተቀር በዚያ ሌላ እንጀራ አልነበረምና።