ዘሌዋውያን 13:45 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “የለምጽ ደዌ ያለበት ሰው የሚለብሳቸው ልብሶች የተቀደዱ ይሁኑ፥ የራሱም ጠጉር የተጐሳቈለ ይሁን፥ ከንፈሩንም ይሸፍን፤ ርኩስ ርኩስ ነኝ እያለ ይጩኽ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እንዲህ ያለ ተላላፊ በሽታ ያለበት ሰው የተቀደደ ልብስ ይልበስ፤ ጠጕሩን ይግለጥ፤ እስከ አፍንጫውም ድረስ ተሸፋፍኖ ‘ርኩስ ነኝ! ርኩስ ነኝ!’ እያለ ይጩኽ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “በዚህ ዐይነት የሥጋ ደዌ በሽታ ያለበት ሰው የተቀዳደደ ልብስ ይልበስ፤ ጠጒሩን አያበጥር፥ ከንፈሩን ይሸፍን፤ ከዚያም በኋላ ‘እኔ የረከስኩ ነኝ! የረከስኩ ነኝ!’ እያለ ይጩኽ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “የለምጽ ደዌ ያለበት ሰው ልብሱ የተቀደደ ይሁን፤ ራሱም የተገለጠ ይሁን፤ ከንፈሩንም ይሸፍን፤ ርኩስ ይባላል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የለምጽ ደዌ ያለበት ሰው ልብሱ የተቀደደ ይሁን፥ ራሱም የተገለጠ ይሁን፥ ከንፈሩንም ይሸፍን፤ ርኩስ ርኩስ ነኝ ይበል። |
ሰውነታቸው የቆዳ በሽታ የያዛቸው አራት ሰዎች ከሰማርያ ቅጽር በር ውጪ ነበሩ፤ እነርሱም እርስ በርሳቸው እንዲህ ተባባሉ፤ “እስክንሞት ድረስ ስለምን በዚህ እንቆያለን?
እኔም፤ “ከንፈሮቼ የረከሱብኝ ሰው ነኝ፤ የምኖረውም ከንፈሮቹ በረከሱበት ሕዝብ መካከል ነው፤ ዐይኖቼም ንጉሡን፤ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርን አይቷልና ጠፍቻለሁ፤ ወዮልኝ!” አልሁ።
ሁላችን እንደ ርኩስ ሰው ሆነናል፥ ጽድቃችንም ሁሉ እንደ መርገም ጨርቅ ነው፤ ሁላችንም እንደ ቅጠል ረግፈናል፥ በደላችንም እንደ ነፋስ ወስዶናል።
ከትንሽነታችን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ እኛና አባቶቻችን በአምላካችን በጌታ ላይ ኃጢአት ሠርተናልና፥ የአምላካችንንም የጌታን ድምፅ አልሰማንምና፥ በእፍረታችን እንጋደም፥ ውርደታችንም ይሸፍነን።”
ሳምኬት። እናንተ ርኩሳን፥ ራቁ፥ ርቃችሁም ሂዱ፥ አትንኩ ብለው ጮኹባቸው። በሸሹና በተቅበዘበዙ ጊዜ፥ በአሕዛብ መካከል፦ በዚህ ከእንግዲህ ወዲህ አይኖሩም ተባለ።
በዝምታ ተክዝ፥ ለሙታን አታልቅስ፤ መጠምጠሚያህን በራስህ ላይ አድርግ፥ ጫማህንም በእግርህ አጥልቅ፤ ከንፈርህን አትሸፍን፥ የዕዝን እንጀራም አትብላ።
ልባችሁን እንጂ ልብሳችሁን አትቅደዱ፥ ጌታ አምላካችሁም ቸርና መሐሪ፥ ቁጣው የዘገየ፥ ጽኑ ፍቅሩ የበዛ፥ ለክፋትም የተጸጸተ ነውና ወደ እርሱ ተመለሱ።
ሙሴም አሮንን፥ ልጆቹንም አልዓዛርንና ኢታምርን እንዲህ አላቸው፦ “እንዳትሞቱ በማኅበሩም ሁሉ ላይ እርሱ እንዳይቈጣ የራሳችሁን ጠጉር አታጐስቁሉ፥ ልብሳችሁንም አትቅደዱ፤ ጌታ እሳትን ልኮ ስላደረገው ማቃጠል ግን ወንድሞቻችሁ የእስራኤል ቤት ሁሉ ያልቅሱ።
“በራሱም ላይ የቅባዓት ዘይት የፈሰሰበት፥ የክህነትም ልብስ እንዲለብስ የተቀደሰው፥ ከወንድሞቹ ይበልጥ ከፍ ያለው ካህን የራሱን ጠጉር አያጐስቁል ልብሱንም አይቅደድ።
“የእስራኤል ልጆች የለምጽ ደዌ ያለበትን ሁሉ፥ ፈሳሽ ነገርም ያለበትን ሁሉ፥ ሬሳንም በመንካት የረከሰውን ሁሉ ከሰፈሩ እንዲያወጡ እዘዛቸው፤